ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት አስመልክቶ የተጠናከረ ዘገባ

በ2027 አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ለሚያደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት የመጀመርያ ልምምዱን መጀመሩ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ከአስር ሰዓት ጀምሮ መደበኛ ልምምዱን ጀምሯል። በዚህም የኢትዮጵያ የእግርኳሱ የበላይ አካል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ምክትላቸው ዶክተር ዳኛቸው ንግሩ እና ዶክተር ሳሙኤል የሸዋስ በብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ ላይ በመገኘት በፕሬዚዳንቱ በኩል ጠንክረው በመስራት ምድቡን የመቀላቀል ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ እስከሚወጣት ጊዜ ድረስ ልምምድ መስራቱን የሚቀጥል ሲሆን ወደ በኋላ ተጨማሪ መረጃ የምናደርሳቹ ይሆናል።
የመጀመርያው ጨዋታ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ
የመረጠችው ሜዳ በሞሮኮ አልጀዲዳ ከተማ በሚገኘው ስታዲየም መሆኑን ተከትሎ የመጀመርያው ጨዋታ መጋቢት አስራ ስምንት በዛ ይከናወናል። ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ አልያም ረቡዕ ወደ ስፍራው ለማቅናት ያሰበ ሲሆን እስካሁን ባገኘነው መረጃ አሁን ባለው ውቅታዊ የአለም ስጋት ምክንያት የጉዞ ሁኔታውን ለማመቻቸት ፌዴሬሽኑን እክል እንደገጠመው የሰማን ሲሆን ሆኖም ባሉት አማራጮች ወደ ስፍራው ለማቅናት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ቡድኑ ከዚህ ቀደም የሚኖሩት የቪዲዮ አናሊስት እና የአካል ብቃት አሰልጣኝ ለጊዜው አሁን የማይኖር መሆኑን አረጋግጠናል። በተያያዘ ዜና በሳውዲ እና በኦማን የሚገኙት ጋቶች እና ከነዓን ሐሙስ መጋቢት አስር እንደሚገቡ ይታወቃል።

