የዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

የዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል


በኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ መካከል የሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና ሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ለሚያደርጉት የቅደመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ሴኔጋላዊው ዳኛ ኤል ሃጂ አማዱ ሲን በዋና ዳኝነት መድቧል። ጨዋታውን የሚመራ የዳኞች ቡድን በሴኔጋላዊያን የተዋቀረ ሲሆን ኤል ሃጂ አማዱ ሲ ዋና ዳኛ፤ ማማዱ ንጎም እና ሙሐመድ ፋል ደግሞ ረዳት ዳኞች እንዲሁም አዳልበርት ዲዮፍ ደግሞ አራተኛ ዳኛ ሆነው ተመድበዋል። የማሊው ማጋሳ ሲዲ ቤካዬም የጨዋታው ኮሚሽነር ሆነው ተሰይመዋል።

ጨዋታው መጋቢት 18 ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በአትላንቲክ የባህር ዳርቻ ላይ በምትገኝው ዋና የወደብ ከተማ ኤል ጃዲዳ በሚገኘው የቤን መሐመድ ኤል አብዲ ስታዲየም ይካሄዳል። ዋልያዎቹ ከዚህ ቀደም በዚህ ስታድየም ባከናወኑት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ጅቡቲን 6 ለ 1 መረምረማቸው ይታወሳል።