ወሳኝ ድል ተቀዳጅቶ ከተመለሰው የዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ አንድ ተጫዋች ተቀላቅሏል።

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የሚሰለጥኑት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን ወደ ሞሮኮ ተጉዞ ኤል-አብዲ ስታዲየም ላይ በከነዓን ማርክነህ እና አቤል ያለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 3-0 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።
ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል በሳውዲ አረቢያ ሁለተኛ ሊግ በአል አረቢያ ስፖርት የሚገኘው እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል የሆነው ጋቶች ፓኖም ከቡድኑ ጋር ተቀላቅሎ ዝግጅቱን ማድረግ በጀመረበት ወቅት በወላጅ አባቱ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ወደ ሞሮኮ ከሚጓዘው ልዑክ ሳይካተት መቅረቱን የዘገብን ሲሆን አሁን ላይ ተጫዋቹ በመልሱ ጨዋታ ሀገሩን ለመወከል ድሬዳዋ ከሚጓዘው ልዑክ ጋር መቀላቀሉን እና እንደሚሄድ ሶከር ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችላለች።
የመልሱ ጨዋታም ማክሰኞ ድሬዳዋ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።

