ግብፃዊያን የኢትዮጵያን ፍልሚያ ሊዳኙ ነው

ግብፃዊያን የኢትዮጵያን ፍልሚያ ሊዳኙ ነው

የፊታችን ማክሰኞ ድሬዳዋ ላይ የሚደረገውን የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ጨዋታ አራት ግብፃዊያን አልቢትሮች እንደሚመሩት ታውቋል።

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሳኦቶሜ አቻውን በመጀመሪያው ጨዋታ 3ለ0 ያሸነፈ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ደግሞ የፊታችን ማክሰኞ ድሬዳዋ ስታዲየም ላይ ያከናውናል።

ወደ ማጣሪያው የምድብ ድልድል የሚያስገባውን ትኬት የሚያስቆርጠው ይህንን የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜና ፕሪንሲፔ ጨዋታም አራት ግብፃዊያን ዳኞች እንደሚመሩት ታውቋል።

በዚህም በመሐል ዳኝነት መሐመድ መዓሩፍ ኢድ ማንሱር ከረዳቶቻቸው ሳሚር ጋማል ሳድ እና አህመድ ታውፊክ ቴሌብ ዓሊ እንዲሁም አራተኛ ዳኘው ማህሙድ አህመድ መሀመድ ባሲዮኒ ጋር ጨዋታውን የሚመሩት ይሆናል።