በትናንትናው ልምምድ ላይ ጉዳት ባስተናገዱት ተጫዋቾች ዙሪያ አዲስ መረጃ ተሰምቷል።

በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው የመጨረሻ የልምምድ መርሐግብር ላይ ጉዳት አጋጥሟቸው ልምምድ አቋርጠው የወጡት ያሬድ ባየህ እና ከነዓን ማርክነህ ለዛሬው ወሳኝ ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል።
በልምምድ ወቅት ከአየር መለዋወጥ ጋር ተያይዞ የአተነፋፈስ ችግር አጋጥሞት የነበረው አማካዩ ከነዓን ማርክነህ ከሕመሙ በፍጥነት በማገገሙ ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑ ተረጋግጧል። በአንጻሩ በልምምድ ወቅት በእግሩ ላይ በደረሰበት ግጭት ምክንያት ለዛሬው ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ መስሎ የነበረው አንበሉ ያሬድ ባየህ በሕክምና ቡድኑ ከፍተኛ ጥረት እና ክትትል ለዛሬው ጨዋታ ብቁ መሆን ችሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ሁለቱም ተጫዋቾች ዛሬ በሚደረገው ጨዋታ ላይ በቋሚነት ሊጀምሩ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ሰምተናል።

