ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ቡና 0-0ድሬዳዋ ከተማ


ጨዋታው 0-0 ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በጩኸት በአሰልጣኙ ላይ ተቃውሞቸውን እየገለፁ ከስቴድየሙ ወጥተዋል።

90+3′ የማያቋርጡ ሙከራዎች በኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች አማካይነት እየተደረጉ በሚያስገርም ሁኔታ እየተሳቱ ነው። ደጋፊው በብስጭት እና በከፍተኛ ልብ መንጠልጠል ውስጥ ይገኛል።

90+1′ ያቡን ዊልያም ከድሬዎች ሳጥን ውስጥ ያገኘውን ኳስ አገባው ሲባል ብዙም ሀይል ያልነበረው በመሆኑ በሳምሶን አሰፋ በቀላሉ ተይዞበታል።

ተጨማሪ ደቂቃ – 5

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
87′ አህመድ ረሽድ ወጥቶ አስናቀ ሞገስ ገብቷል።

86′ ፉአድ ኢብራሂም በመልሶ ማጥቃት ከቀኝ መስመር ያሻገረለትን ኳስ ሀብታሙ ወልዴ ብቻውን ከጎሉ ጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ሞክሮ ሀሪሰን አውጥቶበታል። ስታድየሙን የሞላው ደጋፊን ልብ ቀጥ ያረገ ሙከራ ነበር።

85′ ኢትዮጵያ ቡናዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጭነው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ የድሬደዋዎች መከላከል እና የሳምሶን አሰፋ ብቃትም አስገራሚ ሆኗል።

የተጨዋች ለውጥ – ድሬዳዋ ከተማ
80′ በረከት ይስሀቅ ወጥቶ ፉአድ ኢብራሂም ገብቷል።

78′ ሣለአምላክ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ በግንባሩ ሞክሮ አሁንም ሳምሶን አሰፋ ይዞበታል።

የተጨዋች ለውጥ – ድሬደዋ ከተማ
76′ አሳምነው አንጀሎ ወጥቶ አልሳሃሪ አልማሃዲ ገብቷል።

የተጨዋች ለውጥ – ድሬደዋ ከተማ
73′ ኤርሚያስ በለጠ ወጥቶ ሱራፌል ዳንኤል ገብቷል።

73′ ሳሙኤል ሳኑሚ ከአማኑኤል ዮሀንስ ያገኘውን ኳስ ድሬዎች ሳጥን ውስጥ ሞክሮ ሳምሶን አውጥቶበታል።

71′ ሳለአምላክ ተገኝ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ያቡን ዊልያም ለብቻው ያገኘውን ኳስ በግንባሩ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል። የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችን በቁጭት ያስጮኸ አጋጣሚ ነበር፡፡

70′ አማኑኤል ዮሀንስ ከድሬዎች ሳጥን ጠርዝ ላይ በቀጥታ የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደላይ ወጥቷል። ቡናዎች የተጋጣሚያቸውን የተከላካይ መስመር ለመስበር በሶስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ ብዙ እየጣሩ ነው።

የተጨዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
67′ እያሱ ታምሩ ወጥቶ አብዱልከሪም ሀሰን ገብቷል፡፡

62′ ኤልያስ ማሞ ከቀኝ የማእዘን መምቻ ጋር የተገኘውን ቅጣት ምት አሻማ ተብሎ ሲጠበቅ በድሬዎች ሳጥን ግማሽ ጨረቃ ላይ ለነበረው አማኑኤል ዮሀንስ ሰጥቶት አማኑኤል በቀጥታ ቢሞክርም ሳምሶን አሰፋ ይዞበታል።

58′ ተስፋዬ ዲባባ ኳስ ለማራቅ ሲሞክር እያሱ ታምሩ ተደርቦበት ኳሷን ሳሙኤል ሳኑሚ አግኝቶ ከ ሳጥኑ ጠርዝ ላይ ቢሞክርም ወደላይ ወቶበታል።

የተጨዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
56′ ሳዲቅ ሴቾ ወጥቶ ያቡን ዊልያም ገብቷል፡፡

49′ የድሬደዋ ከተማው አምበል ይሁን እንዳሻው በሁለት የቡና ተጨዋቾች መሀል ገብቶ ከባድ የሚመስል ጉዳት ያስተናገደ ይመስላል። የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ነው።

ተጀመረ!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡
——-
እረፍት!!!
ጨዋታው በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ቡናዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ እና በድሬዎች ጠንካራ መከላከል ቀጥሎ ያለምንም ጭማሪ ደቂቃ የመጀመሪያው ግማሽ ተጠናቋል።

40′ ኤልያስ ማሞ በተስፋዬ ዲባባ ጥፋት ተሰርቶበት ቡናዎች በግምት ከ 25 ሜትር ርቀት ላይ ያገኙትን ቅጣት ምት ራሱ ኤልያስ በቀጥታ መቶ ሳምሶን አሰፋ አውጥቶበታል። በዚህ ሂደት የተሰጠውን የማእዘን ምት ኤልያስ ሞሞ አሻምቶ ሳዲቅ ሴቾ በግንባሩ ሞክሮ ሳምሶን አሰፋ ይዞበታል።

38′ ሔኖክ አዱኛ ከቡናዎች ግብ ክልል በግራ በኩል መሬት ለመሬት ያሻማውን የማእዘን ምት ሀብታሙ ውልዴ አግኝቶ ከግቡ በቅርብ ርቀት ቢሞክርም ሀሪሰን ሄሱ ይዞበታል።

36′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡናዎች የኳስ ቁጥጥር የበላይነት ቢቀጥልም ጠንካራውን እና ወደራሱ ሜዳ በጥልቀት ተጠግቶ የሚከላከለውን የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የተከላካይ እና የማካይ መስመር መስበር የከበዳቸው ይመስላሉ።

29′ በጥሩ የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ኤርሚያስ በለጠ ከ እያሱ ታምሩ ላይ የቀማውን ኳስ ለበረከት ይስሀቅ አሳልፎለት በረከት በቡና ተከላካዮች መሀል ለማለፍ ሲሞክር ኳስ በእጁ ነክቶ ጨዋታው በቅጣት ምት ቀጥሏል።

24′ ኤልያስ ማሞ በግምት ከ22 ሜትር ርቀት የነጠረ ኳስ በቀጥታ አክርሮ ሞክሮ ግብ ጠባቂው ሳምሶን አሰፋ አድኖበታል።

20′ ኤልያስ ማሞ ከድሬዎች መሀል ሜዳ ወደቀኝ አድልቶ የተሰጠውን ቅጣት ምት አሻምቶ ጋቶች ፓኖም በግንባሩ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል።

19′ ከቀኝ መስመር ሔኖክ አዱኛ ወደ መሀል ያሻማውን ኳስ ሀብታሙ ወልዴ በግንባሩ ለማቆጠር ሞክሮ ኳሷ መሬት ነጥራ ስትመለስ ሌላው አጥቂ በረከት ይስሀቅ በመቀስ ምት ሞክሮ ለጥቂት ወደውጪ ወጥቶበታል።

16′ እያሱ ታምሩ ከቀኝ መስመር በቀጥታ ለመሞከር አስቦ የመታው ኳስ ወደላይ ወጥቶበታል።

14′ ኢትዮጵያ ቡናዎች ኳስ በተጋጣሚያቸው ሜዳ ላይ እያንሸራሸሩ ድሬደዋዎች በበኩላቸው ጥንቃቄን መርጠው ጨዋታው ቀጥሏል። የቡና ደጋፊዎች በዳኛው ውሳኔዎች ላይ በተደጋጋሚ ደስተኛ ባለመሆን እየተቃወሙ ነው።

6′ ሳዲቅ ሴቾ ከ ኤልያስ ማሞ የተላከለትን ኳስ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ሞክሮ ግብ ጠባቂው አውጥቶበታል፡፡

3′ እያሱ ታምሩ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ተጠልፌ ወድቅያለው ቢልም የእለቱ አልቢትር በአምላክ ተሰማ በዝምታ አልፈውታል። ደጋፊው ተቃውሞ እያሰማ ነው፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው ተጀምሯል

ለጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር መታሰቢያ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡

የኢትዮጽያ ቡና አሰላለፍ

99. ሀሪሰን ሄሱ

18. ሣለአምላክ ተገኝ — 16. ኤፍሬም ወንድወሰን — 4. ኤኮ ፌቨር — 13. አህመድ ረሽድ

9. ኤልያስ ማሞ — 25. ጋቶች ፓኖም– 8. አማኑኤል ዮሐንስ

7. ሣዲቅ ሤቾ — 11. ሳሙኤል ሳኑሚ — 14. እያሱ ታምሩ

ተጠባባቂዎች

22. ዮሀንስ በዛብህ
5. ወንድይፍራው ጌታሁን
28. ያቡን ዊልያም
17. አብዱልከሪም ሀሰን
27. ዮሴፍ ዳሙዬ
16. እሱባለው ጌታሁን
21. አስናቀ ሞገስ

​የድሬዳዋ ከተማ  አሰላለፍ

1. ሳምሶን አሰፋ

5. ዘሪሁን አንሸቦ – 2. ዘነበ ከበደ – 4. ተስፋዬ ዲባባ (አምበል) – 14. ኄኖክ አዱኛ

24. አሳምነው አንጀሎ — 25. ዘላለም ኢሳይያስ — 6. ይሁን እንዳሻው — 12. ኤርሚያስ በለጠ

18. በረከት ይስሀቅ — 16. ሀብታሙ ወልዴ
 

ተጠባባቂዎች 

23. ቢንያም ሐብታሙ 

17. ፉአድ ሀባስ

19. ፍቃዱ ወርቁ

13. ተስፋዬ ሀይሶ

7. ሱራፌል ዳንኤል

11. በላይ አባይነህ

28. አልሳሃሪ አልማሃዲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *