ካፍ ከ2017-2022 የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው እንዲያገለግሉ አባላትን በጠቅላላ ጉባኤው የሚመርጥ ሲሆን ዛሬ በዕጩነት የቀረቡትን ሰዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፕሬዝደንት የሆኑት ጁነይዲ ባሻ በዝርዝሩ ውስጥ መካተት ችለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ጁይነዲ በመካከለኛው ምስራቅ ዞን ሱዳናዊውን መግዲ ሸምሰዲንን ተክተው የስራ አስፈፃሚ አባል ለመሆን ይወዳደራሉ፡፡ የጁነዲ ተፎካካሪ የሆኑት እራሳቸው መግዲ ሸምሰዲን፣ የዩጋንዳው ሞሰስ ማጎጎ እና የጅቡቲው ሱሌማን ሃሰን ዋቢሪ ናቸው፡፡
ለካፍ ፕሬዝደንትነት ምርጫ ኢሳ ሃያቱን የሚፎካከሩት የማዳጋስካሩ አህመድ ሆነዋል፡፡ አህመድ ለ28 ዓመታት የካፍ ፕሬዝደንት ሆነው የቆዩትን ሃያቱን በልጠው ማሸነፋቸው ቢያጠራጥርም ለውድድሩ ዝግጁ ሆነዋል፡፡
ኢትዮጵያ በካፍ የነበራት ተፅዕኖ ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ካለፉ በኃላ እጅጉን በጣም እንደመቀነሱ አተ ቶጁነይዲ በስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ የመካተት እድል ካገኙ ለኢትዮጵያ እግርኳስ መልካም ዜና ይሆናል፡፡
የሚከተሉት የስራ አስፋፃሚ ኮሜቴ አባላት ዕጩዎች ናቸው፡፡
ሰሜን ዞን
ወጪ አባል፡ መሃመድ ራውራ (አልጄሪያ)
እጩዎች፡ አንዋር ኤል-ታሻኒ (ሊቢያ) ፣ ፋውዚ ሊካ (ሞሮኮ) ፣ መሃመድ ራውራ (አልጄሪያ)
ምእራብ ዞን 1
ወጪ አባል፡ አማዱ ዲያኪቴ (ማሊ)
እጩዎች፡ አማዱ ዲያኪቴ (ማሊ) ፣ ሃሰን ሙሳ ቢሊቲ (ላይቤሪያ)
ምእራብ ዞን 2
ወጪ አባል፡ አንጆሪን ሞቻራፎ (ቤኒን)
እጩዎች፡ አማጁ ፒኒክ (ናይጄሪያ) ፣ አንጆሪን ሞቻራፎ (ቤኒን)
ማዕከላዊ ዞን
ወጪ አባል፡ አንዶም ጂብሪን (ቻድ)
እጩ፡ አንዶም ጂብሪን (ቻድ)
ምስራቅ እና መካከለኛው ዞን
ወጪ አባል፡፡ መግዲ ሸምሰዲን (ሱዳን)
እጩዎች፡ ጁነዲ ባሻ (ኢትዮጵያ) ፣ መግዲ ሸምሰዲን (ሱዳን) ፣ መሰስ ማጎጎ (ዩጋንዳ) ፣ ሱሌማን ሁሴን ዋባሪ (ጅቡቲ)
ደቡብ ዞን
ውጪ አባላት፡ አህመድ (ማዳጋስካር) ፣ ሱኪቱ ፓቴል (ሲሸልስ)
እጩዎች፡ ዳኒ ጆርዳን (ደቡብ አፍሪካ) ፣ ፍራንስ ሚቢዲ (ናሚቢያ) ፣ ሩይ ኤድዋርዶ ዳ ኮስታ (አንጎላ) ፣ ሱኪቱ ፓቴል (ሲሸልስ)