FTወልድያ0-0ድሬዳዋ ከተማ
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው ያለግብ ተጠናቋል፡፡
ቀይ ካርድ
59′ ዳንኤል ደምሴ ከወልድያ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል፡፡
46′ አንዱአለም ንጉሴ እጅግ ግልፅ የሆነ የግብ እድል በማይታመን ሁኔታ አመከነ ፡፡
ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ጎል በአቻ ተጠናቋል፡፡
45+1′ አዱአለም ኑጉሴ በንግባሩ የመታው ኳስ የግቡ አግዳሚ መለሰበት፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ – 2
ቢጫ ካርድ
42″ በድሩ ኑርሁሴን ሆን ብለህ አታለኸኛል በማለት የእለቱ ዳኛ የማስጠንቀቂ ካርድ መዘውበታል፡፡
38′ ምልክቱ ተስተካክሎ ጨዋታው እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡
37′ የማዕዘን መምቻ ምልክት በመገንጠሉ ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል፡፡
35′ ወልድያዎች ጎል ፍለጋ ተጭነው እየተጫወቱ ነው፡፡
23′ የስታድየሙ ፓውዛ ሲበራ ለሜዳው የሚገርም ውበት አላብሶታል፡፡
21′ ጨዋታው ማራኪ የኳስ ፍሰት ቢታይበትም በሁለቱም በኩል ከመሀል ሜዳ ባለፈ ወደ ጎል ለመቅረብ የሚያደርጉት ጥረት እየታየበት አይደለም፡፡
15′ ከስታድየሙ የመግቢያ ዋጋ ጋር ተያይዞ የነበረው የተመልካች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ ህዝቡ በነፃ እንዲገባ በመደረጉ በአሁኑ ሰአት በርካታ ተመልካች እየገባ ይገኛል፡፡
11′ አንዱአለም ንጉሴ ከግራ መስመር ያሻገረውን ቢንያም ዳርሰማ በግንባሩ መትቶ ለጥቂት ወደ ውጭ ወጥቷል፡፡
4′ ዘነበ ከበደ የመታውን ቤሊንጌ ሲተፋው ሀብታሙ ወልዴ ብቻውን አግኝቶ የሞከረውን ኳስ የግቡ ቋሚ መለሰው፡፡
ተጀመረ !!
ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል
11:15 ሁለቱም ቡድኖች ከእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ገዱ አዳርጋቸው እና ዶ/ር አረጋ ይርዳው ከተጨዋቾቹ ጋር በትውውቅ ላይ ናቸው፡፡
የመጀመሪያ አሠላለፍ – ወልድያ ከተማ
16 ኤሚክሪል ቢሌንጌ
3 ቢኒያም ዳርሰማ — 14 ያሬድ ዘውድነህ — 25 አዳሙ መሀመድ — 6 ዮሐንስ ሀይሉ
23 ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ — 18 ዳንኤል ደምሴ — 21 ሀብታሙ ሸዋአለም— 8 ምንያህል ይመር
11 በድሩ ኑርሁሴን — 2 አንዱአለም ንጉሴ
ተጠባባቂዎች
64 ዳዊት አሰፋ
15 ጫላ ድሪባ
4 ሙሉነህ ጌታሁን
28 ታዬ አስማረ
10 ሙሉጌታ ረጋሳ
19 አለማየው ግርማ
20 ነጋ በላይ
የድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ
1. ሳምሶን አሰፋ
2 ዘነበ ከበደ – 4 ተስፋዬ ዲባባ – 15 በረከት ሳሙኤል – 14 ኄኖክ አዱኛ
23 አልሳአሪ አልማሃዲ – 24 አሳምነው አንጀሎ — 6 ይሁን እንደሻው
18. በረከት ይስሀቅ – 16. ሀብታሙ ወልዴ – 7 ሱራፌል ዳንኤል
ተጠባባቂዎች
71 ቢንያም ሀብታሙ
3 ሮቤል ግርማ
10 ረመዳን ናስር
5 ዘሪሁን አንሼቦ
17 ፉአድ አባስ
21 ያሬድ ታደሰ
19 ፍቃዱ ወርቁ