ጅማ አባ ጅፋር አንድ ተጫዋች አስፈርሟል

ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሲሰራ የቆየው ፈሪድ የሱፍ በቋሚ ውል ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሏል

የመስመር አጥቂው ፈሪድ የሱፍ ከዚህ ቀደም የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በሆኑት ቤንች ማጂ ቡና እና ነቀምት ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ከዓመቱ መጀመርያ አንስቶ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሲያደርግ ቆይቶ ነበር።

በአጥቂ ስፍራ ቢስማርክ አፒያ እና ኤርሚያስ ኃይሉን የለቀቀው ጅማ አባ ጅፋር ነገ በሚጀምረው የፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ዙር የአጥቂ መስመሩን በኦኪኪ አፎላቢ እና ፈሪድ የሱፍ አድሶ ይቀርባል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply