የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ጋቦን ለምታስተናግደው የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች የሚደረጉበትን ቀን ይፋ አድርጓል፡፡
በ13 ምድብ ተከፍሎ እየተደረገ ባለው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች እስካሁን ሁለት የጨዋታ መርሃ ግብሮች የተደረጉ ሲሆን የሶስተኛ እና አራተኛ መርሃ ግብር ጨዋታዎች በመጋቢት ወር ይካሄዳሉ፡፡
ከአልጄሪያ፣ ሲሸልስ እና ሌሴቶ ጋር በምድብ 10 የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዓርብ መጋቢት 16 አልጄሪያን አልጀርስ ላይ ይገጥማል፡፡ የመልስ ጨዋታው ከአራት ቀናት በኃላ ማክሰኞ መጋቢት 20 እንደሚደረግ ካፍ አስታውቋል፡፡ በምድቡ ሌላ ጨዋታ ቅዳሜ መጋቢት 17 ሲሸልስ ሌሴቶን ታስተናግዳለች፡፡ የመልስ ጨዋታው መጋቢት 20 ይደረጋል፡፡
ምድቡን አልጄሪያ በ6 ነጥብ ስትመራ ኢትዮጵያ በ4 ትከተላለች፡፡ ሲሸልስ አንድ ነጥብ ሲኖራት ሌሴቶ በምንም ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጣለች፡፡