ባህርዳር ከተማ ቡድኑን በአዲስ መልክ እየገነባ ነው

ጥቅምት 11 ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው የ2010 ዓም የኢትየጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ የሚሳተፈው ባህርዳር ከተማ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ እና ወደ ኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ከአሰልጣኝ ቅጥር ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተጫዋቾችን እያስፈረመ ይገኛል፡፡ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውም ቡድናቸውን እንደ አዲስ እየገነቡ ይገኛሉ፡፡

ቡድኑ እስካሁን 15 ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ዝርዝራቸውና የነበሩበት ክለብ ይህንን ይመስላል፡-

ግብ ጠባቂ
ኃይማኖት አዲሱ (ሱሉልታ ከተማ) ፣ ምንተስኖት አድጎ (ፋሲል ከተማ)

ተከላካዮች
ሰለሞን ብሩ (ጅማ ከተማ) ፣ ሐብታሙ ንጉሴ (አማራ ውሀ ስራ) ፣ ሳላምላክ ተገኝ (ኢትዮጵያ ቡና – ውሰት) ፣ ወንድሜነህ ደረጀ (ሱሉልታ ከተማ) ፣ ያለው ፈንታሁን (ሀድያ ሆሳዕና)

አማካዮች
ኪሩቤል ተካ (ጅማ አባ ቡና) ፣ ባህሩ ከድር (ፌዴራል ፖሊስ) ፣ ፍፁም ክፍሌ (ለገጣፎ) ፣ ደረጀ መንግስቱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ዮናስ በርታን (ለገጣፎ)

አጥቂዎች
እንዳለ ከበደ (ወልዋሎ አዲግራት ዩ.) ፣ ሙሉቀን ታሪኩ (ፋሲል ከተማ) ፣ ወንድማገኝ ግርማ (ለገጣፎ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *