አጫጭር መረጃዎች

የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ያለፉት ሦስት ቀናት ዋና ዋና መረጃዎች ሰብሰብ አድርገን እንዲህ አቅርበነዋል

– በ26ኛ ሳምንት በሲዳማ ቡና እና ደቡብ ፖሊስ መካከል በተደረገው ጨዋታ ላይ የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ረብሻ ፈጥረዋል ያለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 50 ሺህ ብር እና አንድ የሜዳው ጨዋታን ከ200 ኪ/ሜ ርቀት በላይ በሚገኝ ሜዳ እንዲያከናውን ውሳኔ አስተላልፏል።

– በዚሁ በ26ኛ ሳምንት ጅማ ላይ በተደረገው ጨዋታ ላይ ለተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ፌዴሬሽኑ ጅማ አባ ጅፋር 2 የሜዳውን ጨዋታዎች ከ200 ኪ/ሜ በላይ በሚገኝ ሜዳ እንዲያደርግ ወስኗል። ዝርዝር | LINK

– ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ሴቶች ዋንጫ የመጀመርያ ጨዋታዋን ዛሬ መርታለች። ጃፓን ለውድድሩ እንግዳ ቡድን የሆነችው ስኮትላንድን 2-1 የረታችበት ጨዋታን ነው መምራት የቻለችው።

ሊዲያ በጨዋታው ሁለት የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ስትመዝ የጃፓኗ ሱጋሳዋ ያስቆጠረችውን የፍፁም ቅጣት ምትም ወስናለች።

– የኢትዮጵያ ቡና እና የመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ተሸጋግሯል። ጨዋታው ዛሬ በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት ነበር። ዝርዝር | LINK

– የፊፋ/ኮካኮላ ወርሀዊ የዓለም ሀገራት ደረጃ ይፋ ሲደረግ ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ወር በነበረችበት 150ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ቤልጅየም የዓለም ቻምፒዮኗ ፈረንሳይ እና ብራዚልን በማስከተል አሁንም የመጀመርያው ደረጃን ይዛለች።

– ጅማ አባ ጅፋር በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተጣለበትን ቅጣት በተመለከተ ይግባኝ ጠይቋል። ክለቡ ለፌዴሬሽኑ በላከው የይግባኝ ደብዳቤ ለቅጣት ምክንያት ተብለው በፌዴሬሽኑ የተጠቀሱት ሁኔታዎች በጨዋታው ወቅት የተከሰቱትን የማይገልፁ እንደሆኑ በመግለፅ ቅጣቱ ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል።

ፌዴሬሽኑ ጅማ አባጅፋርን ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን በገለልተኛ ሜዳ እንዲያከናውን እና የ100 ሺህ ብር ቅጣት መጣሉ የሚታወስ ነው።

– የአዳማ ከተማዎቹ ሴና እ ዋቁማ እና ሰናይት ቦጋለ ለሙከራ ወደ ስዊድን አምርተዋል። ዝርዝር | LINK