ወልቂጤ ከተማ ለአራት ተጫዋቾች የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

ወጣ ገባ የውድድር ዓመትን እያሳለፈ የሚገኘው አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ ለአራት የቡድኑ ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው የፕሪምየር ሊጉ ስምንት ጨዋታዎች በኋላ ከወራጅ ቀጠናው ደረጃ አንድ ከፍታ ላይ በተቀመጠው ቡድኑ ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች ከአቋም መዋዠቅ እና ክለቡን በተፈለገው ልክ መጥቀም አልቻሉም በሚል ነው የመጀመሪያ ፅሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው። ተጫዋቾቹም ተከላካዩ መሐመድ ሻፊ፣ አማካዩ በቃሉ ገነነ እንዲሁም አጥቂዎቹ ሳዲቅ ሲቾ እና ጃኮ አራፋት ናቸው፡፡

በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርካታ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይገኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: