የአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬው ሽረ ምድረ ገነት ወጣቱን አጥቂ የግሉ አድርጓል
በዝውውር መስኮቱ መክብብ ደገፉ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ በኃይሉ ግርማ፣ ቢኒያም ላንቃሞ እና ፀጋአብ ዮሐንስን ያስፈረሙት ሽረ ምድረ ገነቶች አሁን ደግሞ አጥቂው አቤል ማሙሽን የግላቸው አድርገዋል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የባህርዳር ከተማ ቆይታው በ18 ጨዋታዎች ተሳትፎ 791′ ደቂቃዎች ቡድኑን በማገልገል ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ወጣቱ አጥቂ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ የነበረው ሲሆን ሀምራዊ ለባሾቹ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ሲያድጉም ጉልህ ድርሻ ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን ከባህርዳር ከተማ ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎም ማረፍያው ሽረ ምድረ ገነት ሆኗል።