ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በተጠናቀቀው ውድድር አብሮ የቆየው የመስመር ተከላካያይ ማረፊያው ዐፄዎቹ ቤት ሊሆን ነው።
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን በይፋ ለመሾም የተቃረቡት ዐፄዎቹ የምኞት ደበበ ወል በማራዘም በተጨማሪ ግብ ጠባቂ ሞይስ ፓውቲ እንዲሁም የሁለቱን አጥቂዎች ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ እና ያሬድ ብርሃኑን ዝውውር አስቀድመው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። በመቀጠል ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካዩ አብዱልአዚዝ አማንን ለማስፈረም መቃረባቸው ታውቋል።
በባቱ ከተማ ፕሮጀክት የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው አብዱልአዚዝ በመቀጠል በከፍተኛ ሊግ በቤንች ማጂ ቡና ከተጫወተ በኋላ ያለፈውን አንድ አመት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ቆይታ በማድረግ ራሱን በሊጉ ያስተዋወቀ ሲሆን አሁን ወደ ሌላኘው የሊጉ ክለብ ፋሲል ከነማ ለመጫወት የህክምና ምርመራውን ያጠናቀቀ ሲሆን አመሻሽ ላይ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
