ወልዋሎ የመስመር ተከላካዩን አስፈረመ

ወልዋሎ የመስመር ተከላካዩን አስፈረመ

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በደሴ ከተማ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ወልዋሎ አምርቷል።

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት እና ቀደም ብለው ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃው፣ ኢብራሂም መሐመድ፣ ሰመረ ሀፍታይ፣ ጌትነት ተስፋዬ፣ ፍቃዱ መኮንን፣ ነፃነት ገብረመድህን፣ ሙሉዓለም መስፍን እና ኮንኮኒ ሀፊዝን ለማስፈረም ተስማምተው የኪሩቤል ወንድሙ፣ ናሆም ኃይለማርያም፣ ሱልጣን በርኸ፣ ስምዖን ማሩ፣ ምክኤለ ኪዳኑ፣ ናትናኤል ኪዳነ እና ዳዊት ገብሩን ውል ለማራዘም የተስማሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ተከላካዩ ወጋየሁ ቡርቃን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በተጠናቀቀው ዓመት በከፍተኛ ሊጉ በደሴ ከተማ ቆይታ የነበረውና ለሻሸመኔ ከተማ በፕሪምየር ሊጉ  እና በከፍተኛ ሊግ መወከል የቻለው ይህ ተጫዋች በኢትዮጵያ መድንም ቆይታ የነበረው ሲሆን በቀኝ መስመር ተከላካይነት እና መሀል ተከላካይነት መሰለፍ የሚችል ሁለገብ ተጫዋች ነው።