ከሲዳማ ቡና ጋር ውሉን ለማሰር ተስማምቶ ቅድመ ዝግጅት ገብቶ የነበረው አጥቂው ይገዙ ቦጋለ ሌላ ክለብ ተቀላቅሏል።
ከሳምንታት በፊት በአሳዳጊ ክለቡ ቤት ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ተስማምቶ ቡድኑ ባረፈበት ታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል በመክተም ዝግጅት ሲሰራ የከረመው አጥቂው ይገዙ ቦጋለ ወደ አርሲ ነገሌ ለማምራት ከቡድኑ ጋር እንዲሁ ሲዘጋጅ ቢቆይም የአጥቂው መጨረሻ አርባምንጭ ከተማ ሆኗል።
ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን የተገኘውና ያለፉትን ስምንት የውድድር ዘመናት ለዋናው ቡድን አገልግሎት የሰጠው ይገዙ በ2014 የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን ከዓመታት በኋላ በእግርኳስ ሕይወቱ ሁለተኛ ክለብ ወደ ሆነው አዞዎቹ ለቀጣዮቹ አመታት ለማገልገል ፊርማውን አኑሯል።