ሀዲያ ሆሳዕና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ሀዲያ ሆሳዕና 0-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ
33′ 85′ ሳላዲን ሰኢድ


ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ::

85′ ጎልልል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሳላዲን ከፍጹም ቅጣተት ምት ክልል ውጪ የፈረሰኞቹን 2ኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡

81′ ሳላዲን ከ17 ሜትር ርቀት በግራ እግሩ አክሮ የመታው ኳስ የግቡ አግዳሚ መለሰበት፡፡ ጨዋታው ተሟሙቆ ቀጥሏል፡፡

የተጫዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ
78′
አዳነ ግርማ እና ዘካርያስ ቱጂ ወጥተው ናትናኤል ዘለቀ እና ምንያህል ተሾመ ገብተዋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዲያ ሆሳዕና
75′

ዱላ ሙላቱ ወጥቶ ዎቲሮ ኤልያስ ገብቷል፡፡

57′ አስቻለው ራሱ ግብ ሊያስቆጥር ቢቃረብም ኦዶንካራ በአስደናቂ ሁኔታ አወጣው፡፡

55′ ጊዮርጊሶች ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረውታል፡፡ ወደ ግብ በመድረስም የተሻሉ ናቸው፡፡

52′ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ግብ ጠባቂው ሲተፋው አይዛክ አግኝቶ ቢሞክርም የሀዲያ ተከላካዮች እንደምንም ተረባርበው አውጥተውታል፡፡

48′ ሄኖክ አርፊጮ በቀኝ መስመር የተገኝውን ቅጣት ምት አክርሮ መትቶ ኦዶንካራ ያዘበት፡፡

ተጀመረ!!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ቢጫ ካርድ
44′
አስቻለው ታመነ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ሀድያ ሆሳዕና
41′
ቴዎድሮስ ሁሴን ወጥቶ ኢማኑኤል አኪራሺ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
40′
ራምኬል ሎክ የጨዋታውን የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

* * * በስቴዲዮሙ የሚገኙ ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሆኑ የጊዮርጊስ ደጋፊዎች ደስታቸውን ሲገልፁ አብዛኛው የሜዳው ክፍል በዝምታ ተውጧል፡፡

36′ የግብ ጠባቂውን መውጣት ተከትሎ አዳነ ቺፕ አድርጎ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወጥቷል፡፡ ሌላ ጎል የሚሆን አጋጣሚ ነበር፡፡

ጎልልልልል ቅዱስ ጊዮርጊስ
33′
ሳላዲን ሰኢድ ሁለት ተጫዋቾችን አታሎ በማለፍ ግሩም ግብ አስቆጥሮ ፈረሰኞቹን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

22′ ሳላዲን ከ18 ሜትር ርቀት የተገኘውን ቅጣት ምት ሞክሮ ተከላካዮች ተደርበው አወጡበት፡፡

10′ በሁለቱም በኩል በመሀል ሜዳ ላይ ኳሱን ከማሸራሸር ውጪ እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ ይህ ነው የሚባል የጎል ሙከራ የለም፡፡

ተጀመረ!!!
-ጨዋታው ተጀምሯል፡፡


08:59 ሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ወደ ሜዳ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

08:55 የሁለቱ ቡድን ተጫዋቾች እና ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል እየገቡ ይገኛሉ፡፡

አስገራሚ ክስተት
08:40
የጊዮርጊስ አርማ የታሰረበት በግ እና የሀዲያ ሆሳዕና አርማ የታሰረበት ፍየል ይዞ የመጣ የቅዱስ ጊዮርጊስ የልብ ደጋፊ አስረስ ደባልቄ ለአዳነ ግርማ እና ለእንዳለ ደባልቄ ለመስጠት ቢያስቡም በስቴዲዮም የነበረው ደጋፊ ተቃውሞ በማሰማቱ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

08:20 ሀዲያ ሆሳዕና በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ቢገኝም በስቴዲዮሙ የተገኘው ደጋፊ ብዛት እጅግ በጣም አስደናቂ ነው፡፡


ሀዲያ ሆሳዕና
 
1 ሙሴ ገብረኪዳን

6 ታረቀኝ ጥበቡ – 28 እርቅይሁን ተስፋዬ – 16 ቢንያም ገመቹ – 17 ሄኖክ አርፊጮ

12 ዱላ ሙላቱ – 24 ቴዎድሮስ ሁሴን – 10 ቢንያም ታዬ – 8 ሀይደር ሸረፋ (አምበል)

18 እንዳለ ደባልቄ – 13 አሸናፊ አደም

ተጠባባቂዎች

23 ኄኖክ ወንድማገኝ
21 አልፋየሁ ሙላቱ
22 አድናን ቃሲም
25 ኢማኑኤል አኪራሺ
26 ዎቲሮ ኤልያስ
9 ተመስገን ገብረፃድቅ
 


ቅዱስ ጊዮርጊስ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

5 አይዛክ ኢዜንዴ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 15 አስቻለው ታመነ – 2 መሃሪ መና

18 ራምኬል ሎክ – 21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ – 20 ዘካርያስ ቱጂ

19 አዳነ ግርማ – 10 ሳላዲን ሰኢድ

ተጠባባቂዎች

1 ፍሬው ጌታሁን
4 አበባው ቡታቆ
9 ምንያህል ተሾመ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
17 አቡበከር ሳኒ
15 ጎድዊን ቺካ
26 ናትናኤል ዘለቀ

 


ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን!

የሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስን ይገጥማል፡፡
ሶከር ኢትዮጵያም ጨዋታውን በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከአቢዮ አርሳሞ ስታድየም ታደርሳችኋለች፡፡

መልካም ቆይታ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *