በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው ቡድን ቻምፒዮን ሆኗል

በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው ቡድን ቻምፒዮን ሆኗል

በኢትዮጵያው አሰልጣኝ የሚመራው ካምፓላ ኩዊንስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የፉፋ የሴቶች ካፕ ዋንጫን አንስቷል።

በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው የዩጋንዳው ካምፓላ ኩዊንስ ክለብ ኩዋምፔ ሙስሊም ሌዲስን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የ2026 የፉፋ የሴቶች ካፕ (FUFA Women’s Cup) በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ ሆኗል።

​በፉፋ ስታዲየም ካዲባ በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ላይ የዩጋንዳ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FUFA) ፕሬዝዳንት ክቡር ማጎጎ ሙሴ ሀሲምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተው ነበር።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የሽልማት መርሐግብር ተከናውኖ

የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች እና ከፍተኛ ግብ አግቢ፦ ጆአኒታ አይነምባባዚ (ካምፓላ ኩዊንስ)

​ኮከብ አማካይ፦ ሻሙሳ ናጁማ (ካምፓላ ኩዊንስ)

​ኮከብ ግብ ጠባቂ፦ ሻሮን ኖራ ካይዱ (ካምፓላ ኩዊንስ)

​ኮከብ ተከላካይ፦ ሳማሊ ናካችዋ (ካወምፔ ሙስሊም ሌዲስ)

ሆነው የተመረጡ ሲሆን ይህም የአሰልጣኝ ፍሬው ቡድን ከቡድን ድል በተጨማሪ በግል ስኬቶች ውጤታማ ጊዜ ማሳለፉን ያረጋግጣል።