የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ-ሰሜን ዞን 18ኛ ሳምንት ትላንት እና ዛሬ ተካሂደዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ10 ጨዋታ ያለመሸነፍ ጉዞ በኀላ ለዳሽን እጅ ሲሰጥ ደደቢት ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡ ባንክ እና ኤሌክትሪክ ድል ሲቀናቸው መከላከያም ወደ ማጠቃለያው ውድድር ማለፉን ያረጋገጠበትን ድል አስመዝግቧል፡፡
ትላንት 09:00 ላይ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 4-0 አሸንፏል፡፡ ለኤሌክትሪክ ግቦቹን ፅዮን ፈየራ ፣ እየሩሳሌም ተካ ፣ ታጠርወርቅ ደበሌ እና ዘይነባ ሰይድ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ በ1ኛው ዙርሁለቱ ክለቦች ባደረጉት ጨዋታ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ 4-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡
11:00 የአምናው ቻምፒዮን ንግድ ባንክ ሙገር ሲሚንቶን ገጥሞ 2-0 አሸንፏል፡፡ የሀምራዊዎቹኖ ሁለቱንም የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፈችው ሽታዬ ሲሳይ ናት፡፡
ጎንደር ላይ ዳሽን ቢራ ቅዱስ ጊየዮርጊስን አስተናግዶ 1-0 በማሸነፍ ወየ ማጠቃለያው ውድድር ለማለፍ ተቃርቧል፡፡ የዳሽን ቢራን ብቸኛ የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈችው ሰርክአዲስ ጉታ ናት፡፡
08:00 ላይ ደደቢት ልደታ ክ/ከተማን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል፡፡ ደደቢት 8-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ሎዛ አበራ 4 ግቦች ከመረብ ስታሳርፍ ኤደን ሽፈራው ፣ ሰናይት ባሩዳ ፣ ትበይን መስፍን እና መስከረም ካንክ ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
10:00 ላይ መከላከያ እቴጌን 6-0 በማሸነፍ ወደ ማጠቃለያ ውድድሩ ማለፉን ያረጋገጠ 4ኛው ክለብ ሆኗል፡፡ ከመከላከያ የድል ግቦች አክበረት ገብረፃድቅ እና ተቀይራ የገባችው ምስር ኢብራሂም ሁለት ሁለት ሲያስቆጥሩ እመቤት አዲሱ እና ታደለች አብርሃም ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
*ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሳምንት አራፊ ቡድን ነው፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
በ16ኛ ሳምንት ሳይጫወቱ የቀሩት ኤሌክትሪክ እና ሙገር ሲሚንቶ ማክሰኞ ግንቦት 9 ይጫወታሉ፡፡