ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፡ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ወደ ማጠቃለያው ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ-ምስራቅ ዞን ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንታት እድሜ ብቻ ቀርቶታል፡፡ ዛሬ በተካሄዱ የ8ኛ ሳምንት ጨዋታዎችም ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ለሚያስተናግደው የማጠቃለያ ውድድር ማለፉን አረጋግጧል፡፡ ሲዳማ ቡናም ከድሬዳዋ ከተማ ነጥብ ተጋርቶ ወደ ማጠቃለያው ማለፉን አረጋግጧል፡፡

አዳማ ከተማ ሀዋሳ ከተማን ባስተናገደበት ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እና 9 ግቦች ተስተናግዶበት በሀዋሳ ከተማ 5-4 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ለሀዋሳ ከተማ አይናለም አሳምነው ፣ ዕታለም አመኑ ፣ ሰብለ ቶጋ ፣ ምርቃት ፈለቀ እና አዲስ ንጉሴ ሲያስቆጥሩ አስካለ ገ/ፃድቅ ( 2) ፣ ምህረት ተስፋልዑል እና ገነት ሀይሉ የአዳማን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱ ሀዋሳን ወደ ማጠቃለያው ውድድር ሲያሳልፈው አዳማ ከተማ በሊጉ ግርጌ እንዲቀመጥ አስገድዶታል፡፡

ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማን ገጥሞ ካለ ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ሲዳማ ነጥብ ቢጋራም ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ በመሸነፉ ወደ ማጠቃለያው ዙር ማለፉን ከወዲሁ አረጋግጧል፡፡

አርባምንጭ ከተማ  ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን አስተናግዶ 2-0 አሸንፏል፡፡ የአርባምንጭን የድል ግቦች ሙሉ ሽፈራው እና ፀጋነሽ ኦራ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ሁለት ሳምንት የቀረው ይህ ዞን 4 ክለቦችን ወደ ማጠቃለያው ውድድር ሲያሳልፍ አርባምንጭ እና ድሬዳዋ ማለፋቸውን ያረጋገጡት ሀዋሳ እና ሲዳማ ቡናን ተከትለው ለማለፍ የተሻለ እድል ይዘዋል፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1463335114907

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *