ትናንት ሦስት ተጫዋቾች የቀነሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬም ሌላኛውን የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ጨምሮ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ቀንሷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ መስከረም ወር አጋማሽ ላይ ለሚኖሩበት ሁለት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና በሀዋሳ ከተማ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። ትናንት በግልፅ የታወቁት ታምራት እያሱ፣ ፀጋአብ ግዛው እና አማኑኤል ተርፉ ከቡድኑ ውጭ መደረጋቸው ሲታወቅ ነፃነት ገብረመድን ቡድኑን ያልተቀላቀለ ቢሆንም መቀነሱ እስካሁን እንዳልተነገረው መዘገባችን ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘቸው መረጃ ከሆነ የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ያሬድ የማነህ እና የወቅቱ የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነትን ክብር በጣምራ ማግኘት የቻለው ናትናኤል ዳንኤል ከብሔራዊ ቡድን መቀነሳቸውን ማወቅ ችለናል።

