የስብስቡን ቁጥር እየቀነሰ የሚገኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሁን ደግሞ አንድ ተጫዋች መቀነሱን ሰምተናል

ያለፉትን አራት ሳምንታት በአዲስ አበባ እና በሀዋሳ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ መጨረሻው የዝግጅት ምዕራፍ እየደረሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት ተጫዋቾችን በመቀነስ ላይ ይገኛል።

አስቀድመን ከነገርናችሁ የተቀነሱ ተጫዋቾች በተጨማሪ አሁን ደግሞ የነገሌ አርሲው አማካይ ዳዊት ተፈራ ከብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ መሆኑን አረጋግጠናል።

