የሀዲያ ሆሳዕናው አዲስ ፈራሚ ከብሔራዊ ቡድን ተቀንሷል

የሀዲያ ሆሳዕናው አዲስ ፈራሚ ከብሔራዊ ቡድን ተቀንሷል

ከዋልያዎቹ ስብስብ የተቀነሰው ሰባተኛው ተጫዋች ታውቋል።


አስቀድመን ባደረስናችሁ መረጃ መሠረት ስድስት ተጫዋቾች ከብሔራዊ ቡድኑ ካምፕ መውጣታቸውን የገለፅን ሲሆን አሁን ደግሞ የመጨረሻው ሰባተኛ ተቀናሽ ተጫዋች ታውቋል።

እርሱም ለሀዲያ ሆሳዕና አዲስ ፈራሚ የሆነው ኢዮብ ገብረማርያም መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 22 ተጫዋቾችን ይዞ ዝግጅቱን በሀዋሳ እያደረገ ይገኛል።