በዋልያዎቹ የዛሬ ልምምድ ወሳኙ አጥቂ አልነበረም

በዋልያዎቹ የዛሬ ልምምድ ወሳኙ አጥቂ አልነበረም

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልምምድ ወቅት የመስመር አጥቂው አልተሳተፈም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በቀጣይ ሕዳር ወር ከሞዛምቢክ ጋር ለሚያደርጋቸው 3ኛ እና 4ኛ የምድቡ ጨዋታዎች ትናንት ልምምድ የጀመረ ሲሆን ዛሬ ሁለተኛ ቀን ልምምዱን በአዲስ አበባ ስታዲየም አከናውኗል።

ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾችን መካከል
በኦማን ሊግ የሚገኙት ጋቶች ፓኖም እና ከንዓን ማርክነህ ከቡድኑ ጋር ያለተቀላቀሉ ሲሆን ዛሬ ደግሞ የመቻሉ የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ ከቡድኑ ጋር እንዳልነበረ ዐይተናል።

ሶከር ኢትዮጵያ ቸርነት ትናንት ከቡድኑ ጋር ልምምድ እንደሰራ ስታቅ ዛሬ ያልተገኘበትን ምክንያት ባደረግነው ማጣራት ከጉዳት ጋር በተያያዘ እንደሆነ የሰማን ሲሆን ቀጣይ የተጫዋቹን ሁኔታ ተከታትለን የምንመለስበት ይሆናል።