የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚ ስብስቧን ይፋ አደረገች

የሞሮኮ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጃሚል አይት ቤን ኢዲር ሕዳር 3 በድሬዳዋ ስታድየም ሕዳር 11 ደግሞ በሞውላይ አል ሐሰን ስታድየም ከኢትዮጵያ ጋር ለሚያደርጉት ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ 25 ተጫዋቾችን ያካተተ ስብስብ ይፋ አደረጉ።

ስብስቡ በአውሮፓ፣ በሳዑዲ አረቢያ እና በሞሮኮ በሚገኙ ክለቦች የሚጫወቱ ተጫዋቾች ያካተተ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የዋትፎርዱ አጥቂ ኦስማን ማማ፣ የማላጋው ተከላካይ አዳም አዝኑ እና የአያክሱ ተከላካይ ፋውአድ ዛሁዋኒ ይገኙበታል።
ሞሮኮ በ2023 በራባት በተካሄደው ውድድር በፍፃሜው ጨዋታ ግብፅን 2 ለ 1 አሸንፋ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የውድድሩ ዋንጫ ማሳካቷ የሚታወስ ሲሆን ይህ ስኬትም በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ እንድትሳተፍ አስችሏት በውድድሩ የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።

