የሁለተኛ ቀን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልምምድ ላይ ያልነበረው ቸርነት ጉግሳ ወደ ልምምድ መመለሱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ
ማጣርያ በቀናት ልዩነት ከሞዛምቢክ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች አራተኛ ቀን ልምምድ የጀመረ ሲሆን ልምምዱን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም እየሠራ ይገኛል።
በሁለተኛ ቀን ልምምድ ወቅት የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ በጉዳት ከቡድኑ ጋር አብሮ እንዳልነበረ መዘገባችን ይታወቃል።
ዛሬ ለሚዲያ ክፍት በነበረው የብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ ላይ ቸርነት መመለሱን የተመለከትን ሲሆን የመጀመርያ አስራ አምስት ደቂቃዎችን ከቡድኑ ጋር አብሮ ሲሰራ የተመለከትነው ቢሆኑም በኋላ ላይ ከተከላካይ በረከት ሳሙኤል ጋር ተነጥለው ሜዳውን በሶምሶማ ሲሮጡ ተመልክተናል።
በተለይ ቸርነት ጉግሳ በቀሩት ቀናት የህመሙ ሁኔታ መሻሻል ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ለጨዋታዎቹ ለማድረስ ጥረት እንደሚደረግ አውቀናል።

