ኢትዮጵያ ቡና 1-0 አርባምንጭ ከተማ
75′ አማኑኤል ዮሃንስ
ተጠናቀቀ
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
90+1′ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ወጪ የሞከረውን ኳስ ሀሪሰን ይዞታል፡፡
90′ መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
85′ ጨዋታው በተደጋጋሚ ፊሽካ እየተቋረጠ ይገኛል፡፡ ከግቡ በኋላ ወጥ እንቅስቃሴ መመልከት አልቻልንም፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቡና
78′ ሳዲቅ ሴቾ ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል፡፡
ጎል!! ኢትዮጵያ ቡና
75′ አማኑኤል ዮሃንስ ከግብ ጠባቂው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
67′ ተሾመ ታደሰ ወጥቶ ገብረሚካኤል ያዕቆብ ገብቷል
የተጫዋች ለውጥ – ቡና
64′ መስኡድ እና እያሱ ወጥተው ያቡን እና ዮሴፍ ዳሙዬ ገብተዋል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
56′ አመለ ሚልኪያስ ወጥቶ ምንተስኖት አበራ ገብቷል፡፡
46′ አማኑኤል ዮሃንስ ከርቀት የሞከረውን ኳስ አንተነህ አውጥቶታል፡፡
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡
ቢጫ ካርድ
41′ ትርታዬ ደመቀ አህመድ ረሺድ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
39′ ከሳዲቅ የተሻረለትን ኳስ በጥሩ አቋቋም ላይ እያሱ ሞክሮ አንተነህ በቀላሉ ይዞበታል፡፡
35′ ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታውን ተቆጣጥሯል፡፡ አርባምንጮች በጥልቀት እየተከላከሉ በረጃጅም ኳሶች አደጋ ለመፍጠር እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡
32′ ኤልያስ ማሞ ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
25′ ቡና በኳስ ቁጥጥር የተሻለ ቢሆንም ወደ ግብ በመድረስ አርባምንጮች የተሻሉ ናቸው፡፡
23′ በዛሬው ጨዋታ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በርካታ የአርባምንጭ ከተማ ደጋፊዎች በስታድየም ተገኝተዋል፡፡
20′ ከማእዘን ምት የተሻገረውን ኳስ እንዳለ ከበደ በግንባሩ በመግጨት ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
15′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል፡፡
7′ አመለ ሚልኪያስ ከቀኝ መስመር የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
*** ከስታድየም ውጪ የሚገኙ ደጋፊዎች በሮችን ጥሰው በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በአርባምንጭ አተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
09:53 ተመልካቾች አሁንም ወደ ሜዳ መግባት አልቻሉም፡፡ በመግቢያዎች ላይ የፀጥታ ሃይሎች እና ደጋፊዎች መካከል ግርግር መፈጠር ተጀምሯል፡፡
09:40 ጨዋታው ሊጀመር 20 ደቂቃ ብቻ ቢቀርም ሁሉም የስታድየም በሮች አልተከፈቱም፡፡ ቁጥሩ የበዛ ተመልካች ከስታድየም ውጪ ትኬት ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
1 ሀሪሰን ሄሱ
13 አህመድ ረሺድ – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን- 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 15 አብዱልከሪም መሀመድ
3 መስኡድ መሃመድ (አምበል) – 25 ጋቶች ፓኖም – 9 ኤልያስ ማሞ
24 አማኑኤል ዮሃንስ – 7 ሳዲቅ ሴቾ – 14 እያሱ ታምሩ
ተጠባባቂዎች
99 ወንድወሰን ገረመው
11 ጥላሁን ወልዴ
12 አክሊሉ ዋለልኝ
4 ኢኮ ፊቨ
18 ሳላምላክ ተገኝ
28 ያቡን ዊልያም
27 ዮሴፍ ዳሙዬ
የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ
1 አንተነህ መሳ
2 ወርቅይታደል አበበ – 16 በረከት ቦጋለ – 4 አበበ ጥላሁን – 8 ትርታዬ ደመቀ
7 እንዳለ ከበደ – 18 አማኑኤል ጎበና – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 17 ታደለ መንገሻ
11 አመለ ሚልኪያስ – 23 ተሾመ ታደሰ
ተጠባባቂዎች
70 ጌድዮን መርዕድ
21 ምንተስኖት አበራ
6 ታሪኩ ጎጀሌ
5 ሀብታሙ ወልዴ
13 አስቻለው ኡታ
14 አንድነት አዳነ
19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ