የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ወልድያ ስፖርት ክለብን ከውድድር አገደ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ወልድያ ስፖርት ክለብን ከውድድር ማገዱን ለክለቡ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

የክለቡ ተጫዋቾች የነበሩት ሲሳይ አማረ ፣ ኢዮብ ገብረአረጋዊ እና ድንበሩ መርጊያ ከክለቡ ጋር የፈጠሩትን አለመግባባት ለመፍታት ፌዴሬሽኑ ውሳኔ ቢያሳልፍም ክለቡ ውሳኔውን ተግባራዊ ባለማድረጉ ከማንኛውም የፌዴሬሽኑ ውድድሮች ታግዷል፡፡ ውሳኔውን ተግባራዊ እስከሚያደርግ ድረስም እገዳው እንደሚቀጥል ፌዴሬሽኑ አሳስቧል፡፡ በዚህ መሰረት ክለቡ በፍጥነት ለጉዳዩ እልባት ካልሰጠ በበመጪው ቅዳሜ ሀዋሳ ከተማን የሚያስተናግድበት የ12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሊያልፈው ይችላል፡፡

የወልድያ ስፖርት ክለብ በጉዳዩ ዙርያ ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን ጉዳዩን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል፡፡



በድረገፁ የሚወጡ ፅሁፎች ምንጭ ካልተጠቀስን በቀር ሙሉ ለሙሉ የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ ፅሁፎቹን ለራስዎ ፕሮግራም /ፅሁፍ ሲጠቀሙ ምንጭ ጠቅሰው ይጠቀሙ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *