ሽመልስ በቀለ ቋሚ በነበረበት ጨዋታ ፔትሮጀት አቻ ተለያይቷል 

ኢትዮጵያዊው የአጥቂ አማካይ ሽመልስ በቀለ ቋሚ ሆኖ 90 ደቂቃ በተሰለፈበት የግብፅ ፕሪምየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ጨዋታ ክለቡ ፔትሮጀት ከሜዳው ውጪ ከአረብ ኮንትራክተርስ ጋር 2-2 ተለያይቷል፡፡

በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ አልጄርያን በገጠመችበት ወቅት ዋልያዎቹን በአምበልነት የመራው ሽመልስ ሐሙስ ዕለት በአረብ ኮንትራክተርስ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ቋሚ ሆኖ መሰለፍ ችሏል፡፡ ፔትሮጀት በመሃመድ ራጋብ ሁለት ግቦች ታግዞ ቢመራም መሃመድ ፋድል እና አህመድ አሊ በሁለተኛው አጋማሽ በአራት ደቂቃ ልዩነት ያስቆጠሩት ሁለት ግቦች ለአረብ ኮንትራክተርስ ወሳኝ አንድ ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፔትሮጀት በደረጃ ሰንጠረዡ በ34 ነጥብ 10ኛ ሲሆን ሊጉን ሁለት ጨዋታዎች የሚቀረው የካይሮ ሃያሉ አል አሃሊ በ50 ነጥብ ይመራል፡፡ የከተማ ተቀናቃኙ ዛማሌክ በ41 ነጥብ ሁለተኛ ነው፡፡ የኡመድ ኡኩሪው ኢኤንፒፒአይ ሁለት ቀሪ ጨዋታ እየቀረው በ28 ነጥብ 12ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡ ኢኤንፒፒአይ ከአስዋን ጋር ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ ኢኤንፒፒአይ ባለበት የካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ ጨዋታ ምክንያት ለሌላ ግዜ ተዛውሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *