ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኢትዮጵያ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-1 ኢትዮጵያ ቡና
90+5 ያቤውን ዊልያም (ፍቅም)

ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ጎልልልል!!!! ቡና
90+5 ያቤውን ዊልያም ፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ዊልያም ያቤውን ፍፁም ቅጣት ምቱን ሊመታ ነው፡፡

ፍጹም ቅጣት ምት
ቶክ ጄምስ በግብ ክልሉ ውስጥ በእጁ በመንካቱ የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

88′ አማኑኤል ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

85′ ሁለተኛው አጋማሽ በተለይም ከ60ኛው ደቂቃ በኀላ የግብ ሙከራዎች ያልተስተናገዱበትና የተደራጀ እንቅስቃሴ ያልተደረገበት ሆኗል፡፡

85′ የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
ቢንያም አሰፋ (23) ወጥቶ ናድር ሙባረክ (7) ገብቷል፡፡

83′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
አህመድ ረሺድ (13) ወጥቶ ፓትሪክ ቤናውን (21) ገብቷል፡፡

78′ የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
ሰለሞን ገብረመድህን (8) ወጥቶ ታዲዮስ ወልዴ (18) ገብቷል፡፡

73′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
ኤልያስ ማሞ (9) ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ (12) ወጥቷል፡፡

70′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
ንዳዬ ፋይስ (26) ወጥቶ ሳዲቅ ሴቾ (7) ገብቷል፡፡

61′ ዳንኤል አድሃኖም ከረጅም ርቀት የመታውን ኳስ ሀሪሰን በግሩም ሁኔታ ወደ ውጪ አውጥቶበታል፡፡

60′ ጨዋታው ከመጀመርያው አጋማሽ የተለየ እንቅስቃሴ እየተደረገበት አይደለም፡፡

51′ የአብዱልከሪም የተሻገረለትን ኳስ ፍቅረየሱስ ሞክሮ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

———————
እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

44′ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ ኤፍሬም አሻሞ ሞክሮ ሀሪሰን ይዞበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
42′
ጋቶች በአብዱልከሪም ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

41′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ያቤውን ዊልያም ሞክሮ ግብ ጠባቂው ፌቮ አድኖበታል፡፡

35′ ጨዋታው በጀመረበት ፍጥነት መቀጠል አልቻለም፡፡ የተደራጀ እንቅስቃሴም መመልከት አልቻልንም፡፡

ቢጫ ካርድ
31′
አማኑኤል ዮሃንስ በኤፍሬም በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

23′ ኤልያስ ማሞ ከርቀት መሬት ለመሬት የመታውን ኳስ ኢማኑኤል ፌቮ አውጥቶታል፡፡

20′ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ደቂቃው 20 ሲደርስ የክለቡ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ በመቃወመ ምላይ ይገኛሉ፡፡

ቢጫ ካርድ
13′
አንተነህ ገብረክርስቶስ የመጀመርያውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

8′ በጥሩ ቅብብል የተገኘውን ኳስ አብዱልከሪም ሞክሮ ሀሪሰን ይዞበታል፡፡

6′ ያቤውን ዊልያም ከቀኝ መስመር የሞከረው ኳስ የውጪኛውን መረብ መትቶ ወጥቷል፡፡

5′ ጨዋታው በፈጣን እንቅስቃሴ እና ደማቅ የደጋፊዎች ድባብ ተጀምሯል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በቡና አማካኝነት ተጀመረ፡፡ ባንክ ከግራ ወደ ቀኝ ፤ ቡና ከቀኝ ወደ ግራ ያጠቃል፡፡

11:28 ከመልበሻ ክፍል በመውጣት ሰላምታ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

11:15 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ
1 ኢማኑኤል ፌቮ
98 ዳንኤል አድሃኖም – 16 ቢንያም ሲራጅ – 5 ቶክ ጀምስ – 27 አንተነህ ገብረክርስቶስ
4 ጋብሬል አህመድ – 8 ሰለሞን ገብረመድህን
21 ኤፍሬም አሻሞ – 2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን – 11 አብዱልከሪም መሀመድ
23 ቢንያም አሰፋ

ተጠባባቂዎች
64 ዳዊት አሰፋ
18 ታዲዮስ ወልዴ
26 ጌቱ ረፌራ
7 ናስር ሙባረክ
17 ስንታለም ተሻገር
12 አቤል አበበ
34 አምሃ በለጠ

የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
1 ሀሪሰን ሀሶው
13 አህመድ ረሺድ – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 18 ሳለአምላክ ተገኝ
24 አማኑኤል ዮሃንስ – 25 ጋቶች ፓኖም (አምበል) – 9 ኤልያስ ማሞ
26 ንዳዬ ፋይስ – 28 ያቤውን ዊልያም – 14 እያሱ ታምሩ

ተጠባባቂዎች
99 ወንድወሰን ገረመው
11 ጥላሁን ወልዴ
12 አክሊሉ ዋለልኝ
7 ሳዲቅ ሴቾ
4 ኢኮ ፊቨር
21 ፓትሪክ ቤናውን
3 መስኡድ መሀመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *