ወቅታዊ የውጤት መግለጫ
(ሁሉም 09:00 የጀመሩ ናቸው)
የተጠናቀቀ : ሀዲያ ሆሳእና 1-1 አርባምንጭ ከተማ
43′ ቢንያም ገመቹ | 86′ ተሾመ ታደሰ
የተጠናቀቀ ፡ ወላይታ ድቻ 1-0 ደደቢት
58′ ፀጋዬ ብርሃኑ
የተጠናቀቀ ፡ ሲዳማ ቡና 1-2 ሀዋሳ ከተማ
27′ አንዱአለም ንጉሴ | 22′ ፍርዳወቅ ሲሳይ, 61′ ግርማ በቀለ
የተጠናቀቀ ፡ መከላከያ 2-0 ኤሌክትሪክ
63′ ፍሬው ሰለሞን
69′ ማራኪ ወርቁ
የተጠናቀቀ ፡ ድሬዳዋ ከተማ 3-1 ዳሽን ቢራ
57′ ዮርዳኖስ አባይ, 65′ 74′ ዳዊት እስጢፋኖስ | 68′ ኤዶም ሆሶውሮቪ
———————–
———————–
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በመከላከያ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
90′ መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
84′ ፍፁም ገብረማርያም ወጥቶ ሀብታሙ መንገሻ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
72′ አሳልፈው መኮንን እና በሃይሉ ተሻገር ወጥተው ብሩክ አየለ እነና ትዛዙ መንግስቱ ገብተዋል፡፡
ጎልልል!!! መከላከያ
ባዬ ገዛኸኝ የግብ ጠባቂውን የአቋቋም ስህተት ተከትሎ የሞከረው ኳስ አግዳሚ ሲመልሰው ፍሬው ተቀጣጥሮ ለማራኪ ሲያሻግርለት ማራኪ ወርቁ በጠንካራ ምት የመከላከያን ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ጎልልል!!! መከላከያ
63′ ፍሬው ሰለሞን ከመስመር መሬት ለመሬት የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
61′ ቴዎድሮስ ታፈሰ ወጥቶ ሳሙኤል ሳሊሶ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
57′ ሳሙኤል ታዬ ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል፡፡
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
—-
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡
45′ መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
37′ ባዬ ገዛኸኝ የመታውን ቅጣት ምት አሰግድ በቀላሉ ተቆጣጥሮታል፡፡
34′ ከአሳልፈው የተሻገረውን ኳስ ፍፁም በጥሩ ሁኔታ ቢያመቻችለትም አዲስ ነጋሽ በግቡ አናት ወደ ላይ ሰዶታል፡፡
22′ የመከላከያ እና ኤሌክትሪክ ጨዋታ እስካሁን ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ አልተስተናገደበትም፡፡
ተጀመረ!
በመከላከያ እና ኤሌክትሪክ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ተጀምሯል፡፡
የመከላከያ አሰላለፍ
ጀማል ጣሰው
ታፈሰ ሰርካ – አዲሱ ተስፋዬ – ቴዎድሮስ በቀለ – ነጂብ ሳኒ
ሚካኤል ደስታ – በሃይሉ ግርማ – ፍሬው ሰለሞን – ቴዎድሮስ ታፈሰ – ሳሙኤል ታዬ
ባዬ ገዛኸኝ
የኤሌክትሪክ አሰላለፍ
አሰግድ አክሊሉ
አወት ገ/ሚካኤል – አህመድ ሰኢድ – ሲሴይ ሀሰን – ተስፋዬ መላኩ
በሃይሉ ተሻገር – ደረጄ ሃይሉ – አዲስ ነጋሽ – አሳልፈው መኮንን
ፍፁም ገብረማርያም – ፒተር ኑዋድኬ
– – – – – – / / / ———
ሰላም!
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ዛሬ 6 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም በዋነኝነት በኤሌክትሪክ እና መከላከያ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ላይ ትኩረት በማድረግ የሁሉንም ጨዋታዎች አዳዲስ መረጃዎች ከየቦታው እዚሁ ገፅ ላይ እናቀርብላችኀለን፡፡
መልካም ቆይታ!