የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከሶማልያ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ ጅቡቲ የሚያመሩትን 20 ተጫዋቾች ለይቷል፡፡
በመጀመርያው ጨዋታ የማሸነፍያውን ግብ ያስቆጠረው ተስፋዬ ሽብሩ ባጋጠመው ጉዳት ከጉዞው ሲቀር የመከላከያው ሙጃይድ መሃመድ ፣ የጋምቤላ ከተማው ኡጁሉ ኦክሎ የአአ ዩኒቨርሲቲው ያሲን ጀማል ፣ የቡና ተስፋ ቡድኑ ገናናው እንዲሁም የሰበታ ከተማው ተመስገን ገብረኪዳን የተቀነሱ ተጫዋቾች ናቸው፡-
ወደ ጅቡቲ የሚያቀኑት ተጫዋቾች
ግብ ጠባቂዎች
ተክለማርያም ሻንቆ – አዲስ አበባ
በሽር ደሊል – ሙገር ሲሚንቶ
ምንተስኖት የግሌ – ደደቢት
ተከላካዮች
ዳግም ንጉሴ – ወላይታ ድቻ
ፈቱዲን ጀማል – ወላይታ ድቻ
ሀይደር ሙስጠፋ – ጅማ አባ ቡና
እንየው ካሳሁን – አዲስ አበባ ከተማ
ደስታ ደሙ – ሙገር ሲሚንቶ
ዳንኤል ራህመቶ – አዲስ አበባ ፖሊስ
ኢብራሂም ሁሴን – ሰበታ ከተማ
አማካይ
ኤፍሬም ካሳ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሱራፌል ዳኛቸው – አዳማ ከተማ
ዳዊት ተፈራ – ጅማ አባቡና
ክንዳለም ፍቃዱ – ሙገር ሲሚንቶ
ቢንያም በላይ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሱራፌል ዳንኤል – ድሬዳዋ ከተማ
ዘሪሁን ብርሃኑ – አአ ከተማ
አጥቂዎች
ያሬድ ብርሀኑ – ደደቢት
ኦሜ መሃመድ – ጅማ አባ ቡና
ሱራፌል አወል – ጅማ አባቡና
ብሄራዊ ቡድኑ ከደቂቃዎች በኀላ ወደ ጅቡቲ የሚበር ሲሆን ከሶማልያ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ አርብ ይካሄዳል፡፡