ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፡ ደደቢት ንግድ ባንክን በመርታት መሪነቱን አጠናክሯል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ዙር የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜያቸውን ሲያገኙ ደደቢት ዋንኛ ተቀናቃኙ ንግድ ባንክን ረቷል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከረጅም ወራት በኋላ ድል አግኝቷል፡፡

በ9፡00 ልደታን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና 2-0 በማሸነፍ አንድ ደረጃ አሻሽሏል፡፡ የቡና የድል ግቦች የተገኙት በመጀመርያው አጋማሽ ሲሆን ሎሚ አቡሽ እና ሳራ ይርዳው ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ሁለተኛውን ግብ ከመረብ ያሳረፈችው ሳራ ይርዳው በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴ በማሳየት ለቡና ድል ትልቁን ሚና ተወጥታለች፡፡

PicsArt_1461091019703

11፡00 ላይ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ደደቢት ጨዋታ በደደቢት የበላይነት ተጠናቋል፡፡ በጋምቤላ ክልል በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎቻችን አንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረው ጨዋታ የሜዳ ላይ ሽኩቻዎች እና ውዝግቦች አስተናግዶ በደደቢት 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
image

ደደቢት ቀዳሚ የሆነበትን ግብ ያስቆጠረው ገና በ4ኛው ደቂቃ ነበር፡፡ ሰናይት ቦጋለ ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ (ግማሽ ጨረቃ) በመምታት በግሩም ሁኔታ ደደቢትን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፋለች፡፡ ንግድ ባንኮች ጨዋታውን በመቆጣጠር የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥረው ቢጫወቱም የደደደቢትን የተከላካ መስመር እና በጥሩ አቋም ላይ የምትገኘው ሊያ ሽብሩን አልፈውግብ ሳያስቆጥሩ የመጀመርያው አጋማሽ በደደቢት 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

በ52ኛው ደቂቃ የተገኘውን የቅጣት ምት ሎዛ አበራ ከመረብ አሳርፋ የደደቢትን መሪነት ወደ 2 ስታሰፋ የባንክ ተጫዋቾች የቅጣት ምቱ ካላግባብ ተሰጥቶብናል በሚል ክስ አስመዝግበዋል፡፡ ከግቡ በኋላ ጨዋታው መልኩን ቀይሮ በርካታ ፋውሎች እና የማስጠንቀቂያ ካርዶች ሲታዩ በጨዋታው መጠናቀቅያ ደቂቃዎች ብርቱካን ገብረክርስቶስ በአዳነች በተሰራባት ፋውል ጉዳት አስተናግዳ በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች፡፡

PicsArt_1461090979138

ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች መከላከያ ቅድስት ማርያምን 32 ሲረታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራቸው 9 ግቦች ታግዞ እቴጌን 10-0 አሸንፏል፡፡ ቅዳሜ በተደረገ ብቸኛ ጨዋታ ደግሞ ኤሌክትሪክ ዳሽን ቢራን 1-0 አሸንፏል፡፡

ደደቢት ከ11 ጨዋታ ሙሉ 33 ነጥብ በመሰብሰብ በሰንጠረዡ አናት ሲቀመጥ የአምና ቻምፒዮኑ ንግድ ባንክ በ8 ነጥቦች ርቆ በ25 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ሎዛ አበራ በ27 ግቦች ስትመራ የቅዱስ ጊዮርጊሷ ሄለን ሰይፉ በ19 ትከተላለች፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

image

የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

ቅዳሜ ሚያዝያ 15 ቀን 2008

09፡00 መከላከያ ከ ሙገር ሲሚንቶ (አአ ስታድየም)
09፡00 ዳሽን ቢራ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ጎንደር)
11፡30 ቅድስት ማርያም ዩ. ከ ኤሌክትሪክ (አአ ስታድየም)

እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008

09፡00 ልደታ ከ እቴጌ (አአ ስታድየም)
11፡30 ደደቢት ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *