ደደቢት ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ደደቢት 0-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
17′ ፊሊፕ ዳውዚ

ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በባንክ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90+3′ ሳምሶን በግምት ከ20 ሜትር አክርሮ የመታውን ኳስ ፌቮ አድኖበታል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
90′
ሰለሞን ገብረመድህን ወጥቶ ዳኛቸው በቀለ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
87′
ተካልኝ ደጀኔ ወጥቶ ጆሴፍ አጊዮኪ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
84′
አብዱልከሪም ሀሰን ወጥቶ ታዲዮስ ወልዴ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
82′
አንተነህ ገብረክርስቶስ ተስሎች ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

81′ ከሳምሶን የተሻገረው ኳስ ሳኑሚ በአግባቡ ተቆጣጥሮ የመታውን ኳስ የግቡ አግዳሚ ለትሞ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
77′
ኤፍሬም አሻሞ ወጥቶ ሲሳይ ቶሊ ገብቷል፡፡ ኤፍሬም ሜዳውን ሲለቅ ካለአግባብ ሰአት በማባከኑ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

72′ ሳምሶን በግምት ከ30 ሜትር ርቀት የሞከረውን ኳስ ፌቮ ይዞበታል፡፡

የተጫዋት ለውጥ – ደደቢት
71′
ክዌሲ ኬሊ ወጥቶ ተስሎች ሳይመን ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
69′
ታሪክ ጌትነት ከግብ ክልልሉ ወጥቶ ፍቅረየሱስ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
60′
ጆን ቱፎር በፍቅረየሱስ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተሰጥቶታል፡፡

54′ ሳምሶን ጥላሁን የመታውን የቅጣት ምት በጥሩ ቅልጥፍና ፌቮ አድኖበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
51′
ኤፍሬም አሻሞ የጨዋታውን የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

50′ ፊሊፕ ዳውዚ ከአብዱልከሪም የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀመረ

የእረፍት ሰአት ቅያሪ
ወግደረስ ታዬ ወጥቶ ሄኖክ መኮንን ገብቷል፡፡
– – – – –
እረፍት!!
የመጀመርያው አጋማሽ በባንክ 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

40′ ወግደረስ ታዬ ከማዕዘን የተሻማው ኳስ ሲመለስ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ወጥቷል፡፡

24′ ፊሊፕ ዳውዚ ግቡን ካስቆጠረበት ተመሳሳይ ቦታ የሞከረውን ኳስ ታሪክ እንደምንም አውጥቶታል፡፡

ጎልልል!! ባንክ
17′ ፊሊፕ ዳውዚ የታሪክ ጌትነትን ስህተት ተጠቅሞ ከማዕዘን መምቻ አቅራቢያ ግሩም ግብ አስቆጥሯል፡፡ ግሩም ጎል!

15′ የጨዋታው ፍሰት መልካም ቢሆንም በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ አልተደረገም፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

– – – –
የደደቢት አሰላለፍ
22 ታሪክ ጌትነት
7 ስዩም ተስፋዬ – 15 ጆን ቱፈር – 5 አይናለም ሃይለ – 2 ተካልኝ ደጀኔ
19 ሽመክት ጉግሳ – 32 ክዌሲ ኬሊ – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 10 ብርሃኑ ቦጋለ
9 ወግደረስ ታዬ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ

ተጠባባቂዎች
30 ብርሃኑ ፍስሃዬ
29 ምኞት ደበበ
6 ብሩክ ተሾመ
24 ተስሎች ሳይመን
27 አለምአንተ ካሳ
18 ሄኖክ መኮንን
28 ጆሴፍ አግዮኬ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ
1 ኢማኑኤል ፌቮ
98 ዳንኤል አድሃኖም – 16 ቢንያም ሲራጅ – 5 ቶክ ጀምስ – 27 አንተነህ ገብረክርስቶስ
4 ጋብሬል አህመድ – 8 ሰለሞን ገብረመድህን
21 ኤፍሬም አሻሞ – 2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን – 11 አብዱልከሪም መሀመድ
9 ፊሊፕ ዳውዚ

ተጠባባቂዎች
64 ዳዊት አሰፋ
18 ታዲዮስ ወልዴ
17 ስንታለም ተሻገር
12 አቤል አበበ
19 ሲሳይ ቶሊ
34 አምሃ በለጠ
10 ዳኛቸው በቀለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *