የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ-ምስራቅ ዞን ሁለተኛ ዙር ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡ ጥሩነሽ ዲበባ እና ሲዳማ ቡና ከሜዳቸው ውጪ ድል ሲቀናቸው መሪው ሀዋሳ ከተማም አሸንፏል፡፡
አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን አስተናግዶ 2-0 ተሸንፏል፡፡ በጋምቤላ ክልል በታጣቂዎች በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ በተጀመረው ጨዋታ የጥሩነሽ ዲባባን የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፉት ናርዶስ ጌትነት እና ዮዲት መኮንን ናቸው፡፡
ወደ አርባምንጭ የተጓቸው ሲዳማ ቡና በአርባምንጭ ላይ የ3-0 ድል ተቀዳጅቷል፡፡ የሲዳማ ቡናን ሶስቱንም ግቦች አስቆጥራ ሐት-ትሪክ የሰራችው አይዳ ኡስማን ነች፡፡
ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 4-0 በማሸነፍ መሪነቱን አስጠብቋል፡፡ ትብለፅ አፅብሃ ሁለት ግቦች ስታስቆጥር ፅዮን ሳህሉ እና ምርቃት ፈለቀ ቀሪዎቹን የድል ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
የ7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ቅዳሜ ሚያዝያ 29 ቀን 2008
09፡00 ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ (ሀዋሳ)
09፡00 ድሬዳዋ ከተማ ከ አዳማ ከተማ (ድሬዳዋ)
09፡00 ጥሩነሽ ዲባባ ከ ሲዳማ ቡና (አሰላ)