ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 ኤሌክትሪክ
14′ አዳነ ግርማ
28′ አይዛክ ኢዜንዴ
33′ በሃይሉ አሰፋ
ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው ተጠናቀቀ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመርያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ግቦች ታግዞ 3-0 በማሸነፍ ከተከታዩ አዳማ ከተማ ያለውን ርቀት አሰፍቷል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
85′ ደቂቃዎች በሄዱ ቁጥር ጨዋታው ፍጥነቱ እና ፍሰቱ እየወረደ መጥቷል፡፡ ተጫዋቾች በግል የሚያሳዩት እንቅስቃሴ መድከምም ደጋፊዎችን አላስደሰተም፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
82′ አዳነ ግርማ ወጥቶ ዳዋ ሁቴሳ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
76′ ሳላዲን ሰኢድ ወጥቶ ምንተስኖት አዳነ ገብቷል፡፡
70′ ኤሌክትሪኮች በአንጻራዊነት የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረጉ ቢገኙም የግብ እድሎች መፍጠር አልቻሉም፡፡
*** ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደመጀመርያው አጋማሽ ሁሉ በኳስ ቁጥጥር የተሻለ ሆኗል፡፡ የጨዋታው ፍጥነት እጅግ የወረደ ነው፡፡
61′ ሳላዲን ሰኢድ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ በሃይሉ ሲሞክረው በኤሌክትሪክ ተከላካዮች ተጨርፎ ግብ ለመሆን ለጥቂት ቢተርፍም በቅርብ ርቀት የነበሩት አዳነ እና ጎድዊን ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡
59′ ብሩክ አየለ ከርቀት የመታውን ኳስ ኦዶንካራ ይዞበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
58′ ራምኬል ሎክ (ጉዳት) ወጥቶ ጎድዊን ቺካ ገብቷል፡፡
54′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ አሰግድ ከሳላዲን ቀድሞ ቢያወጣውም በቅርብ ርቀት የነበረው አዳነ ሲመታው ተከላካዮች ከግቡ መስመር አውጥተውታል፡፡
52′ ብሩክ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አይዛክ ጨርፎት ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
ተጀመረ!!!
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
የእረፍት ሰአት ቅያሪ – ኤሌክትሪክ
አህመድ ሰኢድ እና በሃይሉ ተሻገር ወጥተው ትዕዛዙ መንግስቱ እና ተስፋዬ መላኩ ገብተዋል
እረፍት!!!!
የመጀመርያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡
38′ ፒተር ኑዋዲኬ በጥሩ ሁኔታ የመታውን ቅጣት ምት ሮበርት ኦዶንካራ ይዞበታል፡
*** ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁሉም ረገድ ኤሌክትሪክ ላይ ሙሉ ብልጫ ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ፒተር ኑዋዲኬ በግሉ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ውጪ ኤሌክትሪኮች ደካማ እንቅስቃሴ በማሳየት ላይ ይገኛሉ፡፡
35′ ፒተር ኑዋዲኬ ከረጅም ርቀት አክርሮ የመታውን ቅጣት ምት ሮበርት ኦዶንካራ ይዞታል፡፡
ጎልልል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
33′ በሃይሉ አሰፋ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሯል፡፡ ጨዋታው በፈረሰኞቹ ቁጥጥር ስር ሆኗል፡፡
30′ ፒተር ኑዋዲኬ በግምት ከ25 ሜትር አክርሮ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
ጎልልል!!!! አይዛክ ኢዜንዴ
28′ አይዛክ ኢዜንዴ ከቅጣት ምት የቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
24′ አዳነ ግርማ ከመሃሪ በረጅሙ የተላከለትን ኳስ በቮሊ በመመታት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
ጎልልል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
14′ በሃይሉ አሰፋ ያሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ በግንባሩ በመግጨት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
10′ ራምኬል ሎክ በግምት ከ30 ሜትር ርቀት የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
6′ የሲሴይ ሀሰንን ስህተት ተከትሎ አዳነ ግርማ ጥሩ የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ አግኝቶ በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡
ተጀመረ!!!
ጨዋታው በጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡ ጊዮርጊስ ከቀኝ ወደ ግራ ፣ ኤሌክትሪክ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
ሮበርት ኦዶንካራ
አንዳርጋቸው ይላቅ – አይዛክ ኢዜንዴ – አስቻለው ታመነ – መሃሪ መና
ራምኬል ሎክ – ናትናኤል ዘለቀ – ተስፋዬ አለባቸው – በሃይሉ አሰፋ
አዳነ ግርማ – ሳላዲን ሰኢድ
የኤሌክትሪክ አሰላለፍ
አሰግድ አክሊሉ
አወት ገ/ሚካኤል – አህመድ ሰኢድ – በረከት ተሰማ – ሲሴይ ሀሰን
በሃይሉ ተሻገር – ደረጄ ሃይሉ – አዲስ ነጋሽ – ብሩክ አየለ
ፍፁም ገብረማርያም – ፒተር ኑዋድኬ
11:20 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
11:10 ሁለቱም ቡድኖች ከመልበሻ ክፍል ወጥተው በማሟሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡