ድሬዳዋ ከተማ 0-0 ሲዳማ ቡና ፡ ትላንት የተቋረጠው ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ካለ ግብ ተጠናቋል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ትላንት ድሬዳዋ ላይ በድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና መካከል እየተደረገ የነበረው ጨዋታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በእረፍት ሰአት ተቋርጦ የነበረው ጨዋታ ዛሬ ከቆመበት ቀጥሎ እንዳካሄድ ተወስኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጨዋታው 04:00 እንዲደረግ ፕሮግራም ቢያዝም ሜዳው የያዘው ውሃ እስኪደርቅ ተጠብቆ 05:00 ላይ ተካሂዷል፡፡ በዚህም መሰረት 2ኛው 45 የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተካሂዶ ጨዋታው ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ደረጃውን የማሻሻል እድሉን ሳይጠቀምበት ሲቀር ሲዳማ ቡና 1 ደረጃ አሻሽሏል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1461748054731

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *