በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታድየም ተካሂደው ሁለቱም ካለግብ በአቻ ውጤት ተፈፅመዋል፡፡
በ9:00 የተገናኙት መከላከያ እና ደደቢት እጅግ ጥቂት በሆኑ የግብ ሙከራዎች በታጀበ እንቅስቃሴ ካለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በሁለቱም ቡድኖች በኩል የረባ እንቅስቃሴ ባልታየበት ጨዋታ አመዛኙ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በመሃል ሜዳ የተገደበ ሆኖ ውሏል፡፡
የጨዋታው እንቅስቃሴ ሜዳው ላይ ያረፈን አሞራ በትኩረት ምግብ ከመፈለግ እንዲደናቀፍ እንኳን አላደረገም
11:30 ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አርባምንጭ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ ከመጀመርያው ጨዋታ በአንፃራዊነት የተሻለ እንቅስቃሴ ቢታይበትም ግብ ሳይቆጠርበት ተጠናቋል፡፡
አርባምንጭ ከተማዎች በመጀመርያው አጋማሽ የመጨረሻ ደቂቃዎች ከፈጠሩት ተደጋጋሚ ጫና በቀር ጨዋታው ለተመልካች አሰልቺ ነበር፡፡
ትላንት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋርጦ ዛሬ የቀጠለው የድሬዳዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ተመሳሳይ ካለግብ ተጠናቋል፡፡
በ16ኛው ሳምንት ከተደረጉት 7 ጨዋታዎች 4 ጨዋታዎች ካለ ግብ ተጠናቀው ሳምንቱ በግብ ድርቅ እንዲመታ አድርገውታል፡፡
የ16ኛ ሳምንት ውጤቶች
መከላከያ 0-0 ደደቢት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-0 አርባምንጭ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ 0-0 ሲዳማ ቡና
ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 ኤሌክትሪክ
ሀዲያ ሆሳዕና 2-2 ሀዋሳ ከተማ
ወላይታ ድቻ 0-0 ዳሽን ቢራ
አዳማ ከተማ 0-1 ኢትዮጵያ ቡና
የደረጃ ሰንጠረዥ
ከፍተኛ ግብ አግቢዎች
ቀጣይ ጨዋታዎች (17ኛ ሳምንት)
ማክሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2008
09፡00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ድሬዳዋ)
09፡00 ሲዳማ ቡና ከ ሀዲያ ሆሳዕና (ይርጋለም)
09፡00 ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ (ሀዋሳ)
09፡00 ዳሽን ቢራ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ጎንደር)
09:00 ደደቢት ከ አዳማ ከተማ (አአ ስታድየም)
09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ መከላከያ (አርባምንጭ)
11፡30 ኢትዮጵያ ቡና ከ ኤሌክትሪክ (አአ ስታድየም)