የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ 2ኛ ዙር በሳምንቱ መጨረሻ ተጀምሯል፡፡ በዚህ ሳምንት የተደረጉትን ጨዋታዎች እና የደረጃ ሰንጠረዦች ከዚህ በታች ይመልከቱ፡-
ሰሜን ምዕራብ ዞን ምድብ ለ (6ኛ ሳምንት)
እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008
ሰሎዳ አድዋ 4-0 ሽረ እንዳስላሴ (አድዋ)
ደሴ ከተማ 1-0 ዋልታ ፖሊስ (ደሴ)
ሰሜን ምዕራብ ዞን ምድብ ሀ (8ኛ ሳምንት)
እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008
ዳሞት ከተማ 1-2 አምባ ጊዮርጊስ (ፍኖተ ሰላም)
አማራ ፖሊስ 1-1 ጎጃም ደብረማርቆስ (ባህርዳር)
አዊ እምፒልታቅ 1-2 ዳባት ከተማ (እንጅባራ)
ማዕከላዊ ዞን ምድብ ለ (8ኛ ሳምንት)
እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008
አምቦ ከተማ 7-2 ሆለታ ከተማ (አምቦ)
ጨፌ ዶንሳ 0-1 ወሊሶ ከተማ (ጨፌ ዶንሳ)
ወልቂጤ ከተማ 2-0 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ (ወልቂጤ)
ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008
ቦሌ ገርጂ ዩኒየን 0-3 አራዳ ክ/ከተማ (አበበ ቢቂላ)
ደቡብ ምዕራብ ዞን ምድብ ለ (10ኛ ሳምንት)
እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008
አምበሪቾ 1-0 ዲላ ከተማ (አምበሪቾ)
ቡሌ ሆራ 1-0 ጋርዱላ (ቡሌ ሆራ)
ጎፋ ባሬንቾ 0-0 ወላይታ ሶዶ (ጎፋ)
ጎባ ከተማ 1-1 ኮንሶ ኒውዮርክ (ጎባ)
መካከለኛ ዞን ምድብ ሀ (10ኛ ሳምንት)
እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008
ቱሉ ቦሎ 1-0 መቂ ከተማ (ቱሉ ቦሎ)
ለገጣፎ ከተማ ከ ቡታጅራ ከተማ (ለገጣፎ)
-በርካታ የቡታጅራ ተጫዋቾች ህመም ላይ እንደሆኑ ማስረጃ በማቅረባቸው ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል፡፡
ማክሰኞ ሚያዝያ 18 ቀን 2008
ቦሌ ክ/ከተማ 4-1 ዱከም ከተማ (አበበ ቢቂላ)
የካ ክ/ከተማ 0-1 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ (አበበ ቢቂላ)
-አራፊ ቡድን – ልደታ ክ/ከተማ
ምስራቅ ዞን (8ኛ ሳምንት)
እሁድ ሚያዝያ 16 ቀን 2008
ሞጆ ከተማ 2-2 ሐረር ሲቲ (ሞጆ)
መተሃራ ስኳር 5-0 ኢትዮ ሶማሌ ፖሊስ (መተሃራ)
ዓሊ ሐብቴ ጋራዥ 2-4 ወንጂ ስኳር (ድሬዳዋ)
ካሊ ጅግጅጋ ከ ቢሾፍቱ ከተማ (ጅግጅጋ)
የቢሾፍቱ ከተማ አባላት ወደ ጅግጅጋ ሲያመሩ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው በመሆኑ ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡
ደቡብ ምዕራብ ዞን ሀ (6ኛ ሳምንት)
ጋምቤላ ከተማ ከ ዩኒቲ ጋምቤላ (ጋምቤላ)
አሶሳ ከተማ ከ ከፋ ቡና (አሶሳ)
ዩኒቲ ጋምቤላ ከ ሚዛን አማን (ጋምቤላ)
–በዚህ ምድብ ሊደረጉ የነበሩ ጨዋታዎች በጋምቤላ ክልል ባለው ወቅታዊ አለመረጋጋት ምክንያት አልተደረጉም፡፡ ይህ ምድብ 1ኛው ዙር ሲጠናቀቅ የነበረው የደረጃ ሰንጠረዥ ይህን ይመስላል፡-
የቀለማት መግለጫ
–ሰማያዊ ፡ ወደ ማጠቃለያ ውድድር በቀጥታ ለመግባት በሚረዳ ቦታ ላይ የተቀመጡ ቡድኖች
–አረንጓዴ ፡ በጥሩ 3ኝነት ለመግባት የሚረዳ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖች
–ቀይ ፡ ወደ ክልል ሊጎች ለመውረድ በሚያስገድድ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቡድኖች