ኤሌክትሪክ ከ ደደቢት – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኤሌክትሪክ 2-0 ደደቢት
7′ 72′ ፍፁም ገብረማርያም

ተጠናቀቀ!!!!!
ጨዋታው በኤሌክትሪክ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ቀዮቹ ከ4 ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ተመልሰዋል፡፡

90+1′ ዳዊት ፍቃዱ ከርቀት የመታውን ኳስ አሰግድ ይዞበታል፡፡

90′ ፍፁም ገብረማርያም ወጥቶ (ጉዳት) ዋለልኝ ገብሬ ገብቷል፡፡

90′ መደበኛው 90 ደቂቃ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

87′ ዳዊት ፍቃዱ የሞከረውን የቅጣት ምት አሰግድ በግሩም ቅልጥፍና አውጥቶታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
79′
ጆን ቱፎር ወጥቶ ዮሃንስ ፀጋዬ ገብቷል፡፡

78′ ፒተር ኑዋድኬ ከረጅም ርቀት የሞከረው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

75′ ፒተር ኑዋድኬ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ብርሃኔ ይዞታል፡፡

ጎልልልል!!! ኤሌክትሪክ
72′
ፍፁም ገብረማርያም ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅም የኤሌክትሪክን መሪነት ወደ ሁለት አስፍቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
67′
ማናዬ ፋንቱ ወጥቶ አብዱልሃኪም ሱልጣን ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
64′
ማናዬ ፋንቱ በሳምሶን ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

57′ ብርሃኑ ቦጋለ የሞከረውን የቅጣት ምት አሰግድ አክሊሉ አውጥቶታል፡፡

ቢጫ ካርድ
56′
ፍፁም ገብረማርያም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

55′ ማናዬ ፋንቱ ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
49′
ሳኑሚ ኳስ በእጅ በመንካቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

46′ ከመሃል ሜደ ዳየተሻገረውን ኳስ ያሬድ ብርሃኑ ሞክሮ አሰግድ ይዞበታል፡፡

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡

– – – – – –
እረፍት
የመጀመሪያው አጋማሽ በኤሌክትሪክ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

35′ ጨዋታው ላይ የግብ ሙከራዎች እየታዩ አይደለም፡፡ ከሜዳው ውሃ ማዘል ጋር ተያይዞ የሁለቱም ቡድኖች እንቅስቃሴ ከመሃል ሜዳ መዝለል አልቻለም፡፡

30′ ዝናቡ እያየለ መጥቷል፡፡ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴውም ሃይል ያመዘነ ሆኗል፡፡

21′ በመልሶ ማጥቃት የተገኘውን ኳስ ተጠቅሞ ፒተር ኑዋድኬ በግራ እግሩ አክርሮ የመታውን ኳስ ብርሃኔ መልሶታል፡፡

15′ ጨዋታው በዝናብ ታጅቦ እየተካሄደ ነው፡፡ ቀድሞውንም በዝናብ የተበላሸው ሜዳ ኳስ በአግባቡ ለማንሸራሸር አዳጋች ሆኗል፡፡

ጎልልልል!!!! ኤሌክትሪክ
7′
ፍፁም ገብረማርያም ከፒተር ኑዋድኬ የተሻገረለትን ጥሩ ኳስ ተጠቅሞ በግሩም አጨራረስ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ ኤሌክትሪክ ከቀኝ ወደ ግራ ፣ ደደቢት ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡

የኤሌክትሪክ አሰላለፍ
1 አሰግድ አክሊሉ
2 አወት ገ/ሚካኤል – 21 በረከት ተሰማ – 26 ሲሴይ ሀሰን – 15 ተስፋዬ መላኩ
23 ማናዬ ፋንቱ – 4 ማንኮ ክዌሳ – 9 አዲስ ነጋሽ – 10 ብሩክ አየለ
16 ፍፁም ገብረማርያም – 28 ፒተር ኑዋድኬ

ተጠባባቂዎች
22 ገመቹ በቀለ
5 አህመድ ሰኢድ
7 አለምነህ ግርማ
24 ዋለልኝ ገብሬ
27 አሸናፊ ሽብሩ
8 በሃይሉ ተሻገር
17 አብዱልከሪም ሱልጣን

የደደቢት አሰላለፍ
1 ብርሃኔ ፍስሃዬ
29 ምኞት ደበበ – 14 አክሊሉ አየነው – 15 ጆን ቱፎር – 2 ተካልኝ ደጀኔ
99 ያሬድ ብርሃኑ – 21 ሄኖክ ካሳሁን – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 10 ብርሃኑ ቦጋለ
17 ዳዊት ፍቃዱ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ

ተጠባባቂዎች
22 ታሪክ ጌትነት
6 ብሩክ ተሾመ
23 ኄኖክ ኢሳይያስ
90 ዮሃንስ ፀጋዬ
27 አለምአንተ ካሳ
28 ጆሴፍ አግዮኪ
32 ክዌሲ ኬሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *