የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት አንድ ጨዋታ ዛሬ ተደርጎ ኤሌክትሪክ ከተከታታይ ሽንፈቶች ያገገመበትን ድል ደደቢት ላይ አስመዝግቧል፡፡
10:00 ላይ በተጀመረውና በከፍተኛ ዝናብ በታጀበው ጨዋታ ፍጹም ገብረማርያም በ7 እና 72ኛው ደቂቃ የኤሌክትሪክን የማሸነፍያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ውሃ ያዘለው ሜዳ ኳስን ለማንሸራሸር አዳጋች የነበረ ሲሆን ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ ቢደረግበትም የግብ እድል በመፍጠር በኩል ጠንካራ የመከላከል አጨዋወት ይዞ የገባው ኤሌክትሪክ የተሻለ ነበር፡፡
የመጀመርያውን ዙር በጥሩ አቋም ያጠናቀቀው ደደቢት በሁለተኛው ዙር ካደረጋቸው 5 ጨዋታዎች ይህ 3ኛ ሽንፈቱ ነው፡፡ በአንፃሩ ኤሌክትሪክ ከ4 ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል በመመለስ በጊዜያዊነት ከወራጅ ቀጠናው ወጥቷል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
የሊጉ 18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና ሰኞ ይቀጥላሉ፡፡
ቅዳሜ ሚያዝያ 29 ቀን 2008
ኤሌክትሪክ 2-0 ደደቢት (አአ ስታድየም)
እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008
09፡00 አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ (አዳማ)
09፡00 ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና (ቦዲቲ)
09፡00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ሆሳዕና)
10፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)
ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2008
09፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ ስታድየም)
11፡30 መከላከያ ከ ዳሽን ቢራ (አአ ስታድየም)
የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ