ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ኤል ሜሪክ እና ያንግ አፍሪካንስ ድል ቀንቷቸዋል

የ2016 ኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች አርብ ሲጀመሩ የሱዳኑ ኤል ሜሪክ፣ የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ፣ የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እንዲሁም የቱኒዚያው ኤቷል ደ ሳህል ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ኦምዱሩማን ላይ በሜሪክ ስታዲየም የሞሮኮውን ካውካብ ማራካሽን ያስተናገደው ኤል-ሜሪክ 1-0 ማሸነፍ ሲችል ሱዳናዊው የአጥቂ አማካይ ረመዳን አገብ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አዋህዷል፡፡
ዳሬሰላም ላይ ሌላው የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ያንግ አፍሪካንስ የአንጎላውን ሳግራዳ ኤስፔራንሳን ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ከቻምፒየንስ ሊግ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረበት ግብ በአል አሃሊ ተሸንፎ የወደ ምድብ መግባት ላልቻለው ያንጋ ታንዛኒዊያኑ ሳይመን ሙሱቫ እና አንቶኒ ማቲዮ ግቦቹን አስገኝተዋል፡፡

በሳምንቱ አጋማሽ የደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪምየርሺፕን የጌታነህ ከበደውን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፕሪቶሪያን 3-0 በማሸነፍ ለሪከርድ ሰባተኛ ግዜ ዋንጫ ያነሳው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የጋናውን ሚዲአማን 3-1 አሸንፏል፡፡ ሚዲአማ ጨዋታው በተጀመረ በ1ኛው ደቂቃ በኤሪክ ካዋካዋ ግብ መምራት ቢችልም ለሴሌሳኦዎቹ ኮሎምቢያውዊ ሊዮናርዶ ካስትሮ፣ ካሃማ ቢሊአት እና ከትበርት ማላጂላ የድል ግቦቹን የጨዋታው መገባደጃ ላይ አስቆጥረዋል፡፡

image

ኤቷል ደ ሳህል የጋቦኑን ሲኤፍ ሞናናን 2-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ለሶሱ ክለብ የድል ግቦቹን ኤሃብ ሳክኒ እና ዚያድ ቦጋታስ በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡
የአልጄሪያው ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ ከቱኒዚያው ኤስፔራንስ፣ የሊቢያው አል አሃሊ ትሪፖሊ ከ ግብፁ ምስር ኤል ማቃሳ እንዲሁም የማሊው ስታደ ማሊያን ከሞሮኮው ፉስ ራባት በተመሳሳይ 0-0 በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን ጨርሰዋል፡፡
ቀሪ የሶስተኛ ዙር ጨዋታ ዛሬ ሲቀጥል የዲ.ሪ. ኮንጎ ቲፒ ማዜምቤ ሉቡምባሺ ላይ የቱኒዚውን ስታደ ጋቢሲየን ስተናግዳል፡፡

image

የአርብ ውጤቶች
ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ) 2-0 ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን)
አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) 0-0 ምስር ኤል ማቃሳ (ግብፅ)
የቅዳሜ ውጤቶች
ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) 2-0 ሳግራዳ ኤስፔራንሳ (አንጎላ)
ኤል ሜሪክ (ሱዳን) 1-0 ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ)
ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) 3-1 ሚዲአማ (ጋና)
ስታደ ማሊያን (ማሊ) 0-0 ፋት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ)
ሞውሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ 0-0 ኤስፔራንስ ደ ቱኒዚ (ቱኒዚያ)

ፎቶ : ከኤል ሜሪክ ፣ ሞ ቤጃያ እና ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፌስቡክ ገፆች የተገኘ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *