ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 ኢትዮጵያ ቡና

ተጠናቀቀ
ጨዋታው ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

77′ ኤልያስ ማሞ ከሳዲቅ ሴቶ ተመቻችቶ የደረሰዉን ኳስ ሞክሮ በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
72′
ሳላምላክ ተገኝ ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
70′
አስቻለው ታመነ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ቅጣት ምት ለቡና

65′ አዳነ ግርማ የግብ ጠባቂው ሄሱን መዉጣት ተመልክቶ በአየር ላይ የላከዉ ኳስ የግቡን አግዳሚ ታኮ ወደ ዉጭ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
64′
ራምኬል ሎክ ወጥቶ ምንያህል ተሾመ ገብቷል፡፡

51′ አዳነ ግርማ የመታዉን ጠንካራ ቮሊ ሀሪሰን አዳነበት::

46′ ተቀይሮ የገባው ጎድዉን ቺካ ኳሱን ከመስመር እየገፋ ወደ መሀል ገብቶ የሞከረዉ ኳስ ኢላማዉን ሳይጠብቅ ወደ ዉጭ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
በሃይሉ አሰፋ ወጥቶ ጎድዊን ቺካ ገብቷል፡፡

– – – – –
እረፍት!!
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45+2′ ጋቶች ከርቀት የመታዉ ኳስ ወደ ዉጭ ወጥቷል፡፡

45′ መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

43′ ሳዲቅ ሴቶ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭተ ወደ ዉጭ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
34′
አቡዱልከሪም መሀመድ የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

33′ በጨዋታዉ ላይ በርካታ አላስፈላጊ ጥፋቶች በሁለቱም ቡድን ተጨዋቾች በኩል እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

29′ ራምኬል ያሻማዉን ኳስ ሳላዲን ሰኢድ በግንባሩ ቢሞክርም ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

26′ ራምኬል ሎክ ከርቀት ወደ ግቡ የሞከረዉ ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ዉጭ ወጣ፡፡

25′ በጨዋታዉ ወደ ጎል በመድረስ ረገድ ጊዮርጊሶች የተሻሉ ናቸዉ፡፡

18′ ሳላዲን ሰኢድ በግል ጥረቱ የሞከረዉን ኳስ ሀሪሰን ሄሱ ይዞበታል፡፡

15′ ሀሪሰን በመጎዳቱ ምክንያት ጨዋታዉ ለጥቂት ጊዜያት ተቆርጦ ነበር፡፡

12′ አዳነ ግርማ የግብ ጠባቂዉ መውጣትን ተመልክቶ በአየር ላይ የላከዉን ኳስ ፊቨር ኢኮ ከመስመር ላይ አዉጥቶታል፡፡

10′ አህመድ ረሺድ የመታዉን ኳስ ግብ ጠባቂዉ አዉጥቶት የመጀመሪያ የማዕዘን ምት ተገኝቷል፡፡

6′ በሀይሉ አሰፋ ያሻገረዉ ኳስ የጊዮርጊስ አጥቂዎች ከመድረሳቸዉ በፊት ግብ ጠባቂው ሄሱ ይዞታል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና አማካኝነት ተጀመረ

– – – – – –

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
30 ሮበርት ኦዶንካራ
5 አይዛክ ኢዜንዴ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 15 አስቻለው ታመነ – 2 መሃሪ መና
21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ
18 ራምኬል ሎክ – 19 አዳነ ግርማ – 7 በኃይሉ አሰፋ
10 ሳላዲን ሰኢድ

ተጠባባቂዎች
1 ፍሬው ጌታሁን
4 አበባው ቡታቆ
9 ምንያህል ተሾመ
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
17 አቡበከር ሳኒ
16 ጎድዊን ቺካ
26 ናትናኤል ዘለቀ

የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
1 ሀሪሰን ሄሱ
13 አህመድ ረሺድ – 4 ኢኮ ፊቨ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 18 ሳለአምላክ ተገኝ
15 አብዱልከሪም መሀመድ – 25 ጋቶች ፓኖም (አምበል) – 9 ኤልያስ ማሞ
24 አማኑኤል ዮሃንስ – 7 ሳዲቅ ሴቾ – 6 እያሱ ታምሩ
ተጠባባቂዎች

99 ወንድወሰን ገረመው
11 ጥላሁን ወልዴ
12 አክሊሉ ዋለልኝ
5 ወንድይፍራው ጌታሁን
21 ፓትሪክ ቤናውን
3 መስኡድ መሀመድ
27 ዮሴፍ ዳሙዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *