የፕሪሚየር ሊጉ የዝውውር መስኮት መቼ እንደሚከፈት አውቀናል

የፕሪሚየር ሊጉ የዝውውር መስኮት መቼ እንደሚከፈት አውቀናል

ለ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክረምቱ የዝውውር መስኮት መቼ እንደሚከፈት ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረዘም ካሉ ዓመታቶች በኋላ በሃያ ቡድኖች መካከል ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አወዳዳሪነት ካለፉት አምስት አመታቶች በተለየ መልኩ በአንድ ሜዳ ብቻ መደረጉ ቀርቶ በአንድ ቀን በተለያዩ ሜዳዎች ላይ እንደሚደረግ የሚጠበቀው የቀጣዩ የውድድር ዘመን የሀገሪቱ ከፍተኛው የሊግ ዕርከን የመጀመሪያው ዙር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የፋይናንስ ስርዓቱ መጣራት ከተጠናቀቀ በኋላ ይከፈታል ተብሎ የነበር ቢሆንም ከሐምሔ 25/2017 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13/2018 ድረስ እንዲደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መወሰኑን በተለይ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።

በጉዳዩ ዙሪያ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን በቀጣይ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።