በ2018 የክለቦች ክፍያ አስተዳደር ዓመታዊ ጥቅል የገንዘብ መጠን በቀጣይ ሳምንት በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰን ይሆናል።
የሊጉ አክሲዮን ማህበር ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ በ2017 የውድድር ዘመን ተግባራዊ የተደረገ የክለቦችን የክፍያ ጣሪያ አመታዊ ጥቅል ክፍያ 57,750,000 (ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ሆኖ መፅደቁ ይታወሳል። ይህንንም የክፍያን ጣርያ መመርያ ተላልፈዋል በተባሉ 4 በክለቦች እና በ15 ተጫዋቾች ላይ ከበድ ያለ ውሳኔ ተላልፎ እንደነበርም አይዘነጋም።
የ2018 የውድድር ዘመን ሊጀመር ክለቦች ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት ጥረት እያደረጉ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዓመታዊ ጥቅል ክፍያው ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ባለበት ይቀጥላል ወይስ የገንዘቡ መጠን ይጨምራል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል። ለዚህ ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት አክሲዮን ማህበሩም በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አንድ ድምዳሜ ላይ እንደሚደርስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሶከር ኢትዮጵያ ከጠቅላላ ጉባዔው አስቀድሞ እንዳላት መረጃ ከሆነ አብዛኛው ተሳታፊ ክለቦች የገንዘብ መጠኑ ከፍ እንዲል ፍላጎት እንዳላቸው ሰምተናል።