ከአሜሪካ ተጓዡ ቡድን አንድ ባለሙያ እዛው ቀርቷል

ከአሜሪካ ተጓዡ ቡድን አንድ ባለሙያ እዛው ቀርቷል

ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ አሜሪካ ከተጓዘው የቡድኑ ስብስብ ውስጥ አንድ ባለሙያ አለመመለሱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በሚጓዝበት ወቅት ብዙ መወያያና አወዛጋቢ ርዕሶች የማይጣታ ሲሆን ቡድኑም ከትናንት በስትያ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በድል አጠናቆ በአሁኑ ሰዓት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በዋሽግተን ዲሲ ኤርፖርት ይገኛሉ።

ወደ ዩናይትድ ስቴስ ከተጓዙት 31 የልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል አንድ ባለሙያ በዛው መቅረቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። ይህም ግለሰብ የብሔራዊ ቡድኑ የኪት ማናጀር የሆነው አቶ ደምበላሽ እሸቱ(ሻምበል) መሆኑን ሰምተናል።

የዲሲ ዩናይትድ ክለብ መልማዮች የተመለከቷቸው አራት ተጫዋቾች ቢንያም በላይ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ሀብታሙ ተከስተ እና ራምኬል ጀምስ በአሜሪካ MLS እና USL ለመጫወት የሙከራ እድል ያገኙትን ሳይጨምር 27 የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ ይሆናል።