የኢትዮዽያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከጋና ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ዛሬ በዝናባማ አየር ዝግጅቱ ጀምሯል፡፡
ቡድኑ ለሶማልያው ጨዋታ ዝግጅት ላይ ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል 9 በመቀነስ 12 አዳዲስ ተጫዋቾችን በመጥራት በአጠቃላይ 29 ተጫዋቾችን ይዟል፡፡
ቡድኑ በዝግጅት እና የወዳጅነት ጨዋታዎች የተጫዋቶችን ብቃት በማየት ከቀናት በኋላ ስብስቡን ወደ 25 ዝቅ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለዚህ እንዲረዳም ነገ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ጋር ይጫወታሉ፡፡
በዛሬው ልምምድ ላይ 26 ተጨዋቾች ልምምድ የሰሩ ሲሆን የጅማ አባቡናው አጥቂ ሱራፌል አወል ጥርሱ ጥርሱ ላይ ባጋጠመው መጠነኛ ጉዳት ዛሬ ልምምድ ያልሰራ ቢሆንም በቅርብ ቀን ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ታውቋል፡፡ ደስታ ዮሃንስ ፣ አቡበከር ሳኒ እና ዳዊት ማሞ ደግሞ ጥሪው የደረሳቸው ዛሬ በመሆኑ ነገ ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለው ልምምድ እንደሚጀምሩ ተነግሯል፡፡
የዛሬው ልምምድ በሁለት ተከፍሎ የተደረገ ሲሆን ነባሮቹ 17 ተጫዋቾች ተለይተው ቀላል ልምምድ አድርገዋል፡፡ አዲስ የተጠሩት 9 ተጫዋቾች ደግሞ ለሁለት ተከፍለው ግማሽ ሜዳ ተጫውተዋል፡፡
** የቡድን ዝርዝር
ግብ ጠባቂዎች
ተክለማርያም ሻንቆ – አዲስ አበባ
በሽር ደሊል – ሙገር ሲሚንቶ
ምንተስኖት የግሌ – ደደቢት
ተከላካዮች
ፈቱዲን ጀማል – ወላይታ ድቻ
ሀይደር ሙስጠፋ – ጅማ አባ ቡና
እንየው ካሳሁን – አዲስ አበባ ከተማ
ደስታ ደሙ – ሙገር ሲሚንቶ
ዳንኤል ራህመቶ – አዲስ አበባ ፖሊስ
ኢብራሂም ሁሴን – ሰበታ ከተማ
ዳግም ንጉሴ – ወላይታ ድቻ
አማካዮች
ኤፍሬም ካሳ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሱራፌል ዳኛቸው – አዳማ ከተማ
ዳዊት ተፈራ – ጅማ አባቡና
ዘሪሁን ብርሃኑ – አአ ከተማ
ክንዳለም ፍቃዱ – ሙገር ሲሚንቶ
ምስጋናው ወ/ዮሐንስ – ደቡብ ፖሊስ (አዲስ የተመረጠ)
ኪዳኔ አሰፋ – ጅማ አባ ቡና (አዲስ የተመረጠ)
ደስታ ዮሐንስ – ሀዋሳ ከተማ (አዲስ የተመረጠ)
አቡበከር ሳኒ – ቅዱስ ጊዮርጊስ (አዲስ የተመረጠ)
ዳዊት ማሞ – አአ ከተማ (አዲስ የተመረጠ)
ሚካኤል ለማ – ደቡብ ፖሊስ (አዲስ የተመረጠ)
ፀጋ ጎሳዬ – ሻሸመኔ ከተማ (አዲስ የተመረጠ)
ብርሃኑ በቀለ – ሻሸመኔ ከተማ (አዲስ የተመረጠ)
(ቢንያም በላይ ቢመረጥም በጉዳት ከቡድኑ ውጪ ሆኗል)
አጥቂዎች
ኦሜ መሃመድ – ጅማ አባ ቡና
ሱራፌል አወል – ጅማ አባቡና
ያሬድ ብርሃኑ – ደደቢት
ሀብታሙ ገዛኸኝ – ደቡብ ፖሊስ (አዲስ የተመረጠ)
ዘላለም ኢሳያስ – ደቡብ ፖሊስ (አዲስ የተመረጠ)
ውብሸት ስዮም – ሻሸመኔ ከተማ (አዲስ የተመረጠ)
ጫላ ተሻገር – ሻሸመኔ ከተማ (አዲስ የተመረጠ)
የተቀነሱ ተጫዋቾች
ተስፋዬ ሽብሩ – አአ ፖሊስ (ጉዳት)
ሙጃይድ መሃመድ – መከላከያ
ኡጁሉ ኦክሎ – ጋምቤላ ከተማ
ያሲን ጀማል – አአ ዩኒቨርሲቲ
ገናናው – ኢትዮጵያ ቡና (ተስፋ)
ተመስገን ገብረኪዳን – ሰበታ ከተማ
ቢንያም በላይ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ጉዳት)
ሱራፌል ዳንኤል – ድሬዳዋ ከተማ