አዲሱ የቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ካፕ ደንብ ለኢትዮጵያ መልካም ዜና ይዞ ይመጣ ይሆን?

በ2017 የቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽንስ ዋንጫዎች የምድብ ቁጥራቸው ከ2 ወደ አራት ያድጋል፡፡

በአፍሪካ የክለቦች ዓመታዊ ውድድር የሆኑት የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ቁጥር አሁን ካለበት ሁለት ወደ አራት ከፍ ማድረጉን የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን ዛሬ አስታውቋል፡፡
እንደ ካፍ ገለፃ ከሆነ ውሳኔው ተግባራዊ የሚሆነው ከ2017 የውድድር ዘመን ጀምሮ እንደሆነ ሜክሲኮ መዲና ሜክሲኮ ሲቲ በተደረገው የካፍ 38ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ውሳኔውን ያሳወቁት ፕሬዝደንቱ ኢሳ ሃያቱ ናቸው፡፡
ለረጅም ዘመናት ካፍ ቻምፒየንስ ሊጉን እና ኮንፌድሬሽን ካፑ በሁለት የተገደበ ምድቦች ምክንያት ወቀሳ ሲቀርብበት የነበረ ሲሆን አሁን የምድብ ቁጥሩን ወደ አራት ከፍ አድርጓል፡፡ ወደ ቻምፒየንስ ሊጉን ምድብ ለመግባት አንድ ክለብ ቢበዛ ቅድመ ማጣሪያውን እና የአንደኛ ዙር ማጣሪያ ዙር መጫወት ይጠበቅበታል፡፡ የምድብ ቁጥሩ ወደ አራት ማደግም የሁለተኛ ዙር ማጣሪያን የሚያስቀር ይሆናል፡፡ የቻምፒየንስ ሊጉን አንደኛ ዙር ማለፍ የሚያቅታቸው ክለቦች ደግሞ ወደ ኮንፌድሬሽን ካፑ የሚወርዱ ይሆናል፡፡ ኮንፌድሬሽን ካፑ ልክ እንደቻምፒየንስ ሊጉ ሁሉ አራት ምድብ ይኖረዋል፡፡
ፊፋ የጀመረው የለውጥ ጎዳና ካፍን ወደ ውሳኔው እንደሚመጣ ያስገደደው ይመስላል፡፡ የቻምፒየንስ ሊጉ እና ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ማጣሪያ ውስጥ መግባት ለሚያስቸግራቸው ለአብዛኞቹ የምስራቅ አፍሪካ ክለቦች (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ይህ ውሳኔ አስደሳች ይመስላል፡፡ ካፍ ቻምፒየንስ ሊጉን እንደአዲስ ካወቀረበት ከ1997 ግዜ ጀምሮ አንድም የኢትዮጵያ ክለብ ወደ ምድብ አልፎ አያውቅም፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2013 በዛማሌክ በአጠቃላይ ውጤት ተሸንፎ ወደ ምድብ ሳይገባ መቅረቱ ይታወሳል፡፡ ኀላ ላይ ወደ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቱለተኛ ዙር የገባው ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን ወክሎ በምድብ ማጣሪያ የተሳተፈው ብቸኛ ክለብ ነው፡፡
በወቅቱ ጊዮርጊስ ስታደ ማሊያን፣ ሲኤስ ሴፋክሲየን እና ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል በሚገኙበት ምድብ በአራት ነጥብ የምድቡን ግርጌ በመያዝ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

(ኮንፌድሬሽን ካፕ የተጀመረው በ2004 ካፍ ካፕ እና አፍሪካን ካፕ ዊነርስ ካፕ በማቀናጀት ነበር)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *