በዐፄዎቹ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ሽረ ምድረ ገነትን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።
ወደ ዝውውሩ ዘግይተው የገቡትና ባለፉት ቀናት መክብብ ደገፉ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ በኃይሉ ግርማ እና ፀጋአብ ዮሐንስን ለማስፈረም የተስማሙት ሽረ ምድረ ገነቶች አሁን ደግሞ በዝውውር መስኮቱ አምስተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል፤ ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ደግሞ ቢንያም ላንቃሞ ነው።
በተጠናቀቀው የዉድድር ዓመት በሁለት ዓመት ዉል ፋሲል ከነማን ተቀላቅሎ ከቡድኑ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት የተለያየው የመስመር ተጫዋቹ በዐፄዎቹ የአንድ ዓመት ቆይታው በ19 ጨዋታዎች ተሳትፎ 1160′ ደቂቃዎች ቡድኑን በማገልገል ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል። ተጫዋቹ ከሲዳማ ወጣት ቡድን በኋላ በመቻል፣ ወልዲያ ከተማ እንዲሁም ፋሲል ከነማ መጫወቱ ይታወሳል፤ አሁን ደግሞ የሽረ ምድረገነት አምስተኛ ፈራሚ ለመሆን ከስምምነት ደርሷል።